Dehai News

Ethsat.com: በኦሮሚያ ኢሊባቦር በጮራ ወረዳ ቦሮ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው አማሮች መገደላቸው ተሰማ

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Monday, 23 October 2017

በኦሮሚያ ኢሊባቦር በጮራ ወረዳ ቦሮ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው አማሮች መገደላቸው ተሰማ

Watch: ESAT Daily News Amsterdam October 23,2017

https://www.youtube.com/watch?time_continue=53&v=OBjRBdWFqsY

23/10/2017

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 13/2010) በኦሮሚያ ኢሊባቦር በጮራ ወረዳ ቦሮ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው አማሮች መገደላቸውንና መፈናቀላቸውን የኢሳት የአካባቢው ምንጮች ገለጹ።

በአካባቢው የሚኖሩ አማሮች ቤታቸው ተቃጥሎ፣ንብረታቸው ወድሞ የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው።

የሚሸሹበት መንገድ ስለተዘጋባቸውም ሕጻናትና ሴቶች እንዲሁም ሽማግሌዎች በረሃብና በጥም እየተሰቃዩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በሕወሃት መራሹ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም ምክንያት የብሔር ግጭትን ማራገብ ከተጀመረ 26 አመታት ተቆጥሯል።

በዚሁ የጎሳ ፖለቲካ ምክንያት በርካታ አማሮች ከኦሮሚያ ክልል ሲፈናቀሉ፣ሲገደሉና ሲጨፈጨፉ ቆይተዋል።

በሌሎች ክልሎችም በጉራፈርዳና በቤንሻንጉል ተመሳሳይ ግድያና ፍንቀላ ሲካሄድ ነው የነበረው።

አሁን ዳግም በኦሮሚያ ኢሊባቦር በጊዲጋና ጮራ ወረዳዎች በተለይም ቦሮ ጮራ የተባለች ከተማ በርካታ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች ሲገደሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል።

በጫካ ውስጥ የተደበቁትና ሕይወታቸውን ለማትረፍ የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ያሉት የአማራ ተወላጆች ሕጻናት፣ሴቶችና ሽማግሌዎች በረሃብ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ለኢሳት ተናግረዋል።

ግድያውና ማፈናቀሉ አካባቢውን ልቀቁ በሚል በኦሮሞ ወጣቶች የሚመራ እንደሆነ ተጎጂዎቹ ይናገራሉ።

ይህ ሁሉ ግድያና መፈናቀል ሲደርስም የኦህዴድ አካላት ምንም አይነት ርምጃ አለመውሰዳቸውን ነው የገለጹት።

እናም መውጫና መድረሻ ያጡትን ቀሪ የአማራ ተወላጆች ለማትረፍ ምንም አማራጭ ስለሌለ በብአዴን የሚመራው መንግስት እንዲደርስልን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ብለዋል።

የሟቾችን ቁጥር ለማወቅ እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነም ጉዳቱ የደረሰባቸው የአማራ ተወላጆች ይገልጻሉ።

ጉዳዩን አስቸጋሪ ያደረገው ደግሞ ከሟቾቹ 10ሮቹን ብቻ ለመቅበር ቢችሉም የሌሎቹን አስከሬን ግን ለመቅበር ስላልተፈቀደላቸው ራሳቸው ጥቃት ፈጻሚዎቹ ወስደው መቅበራቸውን ተጎጂዎቹ ገልጸዋል።

ለዚህ ሁሉ ጅምላ ግድያ ተጠያቂው ማን ነው በሚል ላነሳነው ጥያቄ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ የኦህዴድ አካላት መሆናቸውን ነው የገለጹት።

ተጎጂዎቹ የአማራ ተወላጆች እንዳሉት ለዘመናት አብረን ከኦሮሞዎች ጋር የኖርን ሰዎች እንዴት በአንድ ጊዜ ጥቃት ይደርስብናል ሲሉም ይጠይቃሉ።

የዚህ ሁሉ መንስኤም የሕወሃት ብሄር ተኮር ፖለቲካ መሆኑን ደግሞ የፖለቲካ ተንታኞች እየተናገሩ ይገኛሉ።


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events