Dehai News

(ሪፖርተር) ለእረፍት የተበተነው ፓርላማ ለአስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ መሆኑ ተሰማ፣የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ስምምነትን ማፅደቅ ቀዳሚ አጀንዳው እንደሚያደርግ ይጠበቃል

Posted by: Semere Asmelash

Date: Wednesday, 11 July 2018



  1. ለእረፍት የተበተነው ፓርላማ ለአስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ መሆኑ ተሰማ
ለእረፍት የተበተነው ፓርላማ ለአስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ መሆኑ ተሰማ

ለእረፍት የተበተነው ፓርላማ ለአስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ መሆኑ ተሰማ

የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ስምምነትን ማፅደቅ ቀዳሚ አጀንዳው እንደሚያደርግ ይጠበቃል

ቅዳሜ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የዓመቱን የሥራ ጊዜ አጠናቆ ለእረፍት የተበተነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በቅርቡ ለአስቸኳይ ስብሰባ እንደሚጠራ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡

ምክር ቤቱ የዓመቱን የሥራ ጊዜውን አጠናቆ ለሦስት ወራት እረፍት በይፋ የተበተነ ቢሆንም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ የሚጠራ በመሆኑ የምክር ቤቱ አባላት ከአዲስ አበባ ርቀው እንዳይሄዱ የተነገራቸው መሆኑን ምንጮች አክለዋል፡፡

በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ ‹‹ምክር ቤቱ በእረፍት ላይ እያለ የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚሹ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ አስቸኳይ ሊጠራ ይችላል፤›› በማለት የሚደነግግ ሲሆን፣ በንዑስ አንቀጽ 2 ሥር ደግሞ ምክር ቤቱ እረፍት ላይ በሚሆንበት ጊዜ አፈ ጉባዔው ወይም ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የምክር ቤቱ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ከጠየቁ፣ አፈ ጉባዔው የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡

በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ መሠረት አስቸኳይ ስብሰባ የሚጠራው በአመዛኙ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲፀድቅለት የሚጠይቀው ሁኔታ ሲፈጠር እንደሆነ የገለጹት ምንጮች፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰሞኑን ኤርትራን በመጎብኘት በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረው የተበላሸ ግንኙነት እንዲያበቃና በወዳጅነት ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንዲጀመር፣ የሁለቱ አገሮች መሪዎች የደረሱበት ስምምነት በአስቸኳይ ስብሰባ ለፓርላማው ሊቀርብ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በአስመራ ባደረጉት ስምምነት በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረው የጦርነት ሁኔታ (State of War) እንዲያበቃና አዲስ የሰላምና የወዳጅነት ምዕራፍ እንዲጀመር፣ የሁለቱ አገሮች ሕዝቦችን ጥቅም ለመጠበቅና የበለጠ ለማሻሻል ሁለቱ መንግሥታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በባህላዊና በደኅንነት ጉዳዮች ላይ ተባብረው እንደሚሠሩ፣ የትራንስፖርት፣ የንግድና የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቶች እንዲጀምሩ፣ የተቋረጠው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲቀጥል፣ የድንበር ውሳኔውን ተፈጻሚ ለማድረግና በአካባቢያዊ የሰላምና ልማት ጉዳዮችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የስምምነቱ አራት ነጥቦች በጥቅሉ ተጨምቀው የመሪዎቹ ፊርማ ያረፈበት ቢሆንም፣ እያንዳንዱ የስምምነት ነጥብ በመዘርዘር ሕግ ሆኖ በሁለቱም አገሮች እንዲፀድቅ የማድረግ ተግባር የሚከተል መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ለዓብነት ሲያስረዱም በመሪዎቹ ስምምነት በተራ ቁጥር ሦስት ሥር ሁለቱ አገሮች በትራንስፖርት፣ በንግድና በቴሌኮሙዩኒኬሽን ግንኙነታቸውን እንዲቀጥሉ የቀረበው ጥቅል ሐሳብ ሲዘረዘር ሰፊ ነው ይላሉ፡፡

በዚህ ውስጥ የአየር ትራንስፖርት ግንኙነት፣ የየብስ ትራንስፖርት ግንኙነት፣ ንግድን በተመለከተ ያለው ደግሞ እስከ ወደብ ኪራይ ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን በመጠቆም፣ በእያንዳንዱ የስምምነት ጥቅል ሐሳቦች ሥር በርካታ አዋጆች እንደሚወጡ ምንጮች አስረድተዋል፡፡

በአስቸኳይ የሚጠራው ፓርላማ ከተገለጸው አጀንዳ ውጪ በይደር ያቆያቸውን የስደተኞች ጉዳይ አዋጅና የምሕረት መስጫ አዋጅ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለእረፍት የተበተነው ፓርላማ ለአስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ መሆኑ ተሰማ




7ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 7 - ERi-TV Documentary

Dehai Events