ከሀያ አመታት በላይ ሰላም በማጣት ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚያገናኘው መንገድ እየተከፈተ መሆኑን ከሁመራ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

በዛላንበሳና በራማ በኩልም ተመሳሳይ ሁኔታ እንዳለ ነው የተሰማው።

መንገዶቹ ዛሬ በወጣቶች ጉልበት ድንጋዮችና ጋሬጣዎች የተነሱ ሲሆን የመንግስትን ይሁንታ ያገኘ ይሁን አይሆን የታወቀ ነገር የለም።