Dehai News

Dahabshiil long banner 728x90
Eritrea for mobile viewing

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ የሶስትዮሽ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Thursday, 06 September 2018

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ የሶስትዮሽ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ የሶስትዮሽ ቀጠናዊ ትስስራቸውን የሚያጠናክር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር እብይ አህመድ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዲላሂ በኤርትራ አስመራ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ሶስቱ መሪዎች በነበራቸው ቆይታም በተለያዩ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ከተወያዩ በኋላ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደርሰዋል።

በዚሁ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር እብይ አህመድ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዲላሂ የሶስቱን ሀገራት ቀጠናዊ ትስስር የሚያጠናክር የሶስትዮሽ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።
 
ሶስቱ መሪዎች በደረሱት ስምምነት መሰረትም የሀገራቱን ህዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ ትብብር፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በባህል፣ በማህበራዊ እና በደህንነት ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራትን ያካተተ ነው።
 
እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ በትብብር ለመስራትም ከስምምነት ደርሰዋል።
 
ስምምነታቸውን ወደ ተግባር ለመቀየር በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ የተዋቀረ ኮሚቴም ለማቋቋም ተስማምተዋል።
 
መሪዎቹ አክለውም በኤርትራ እና በጂቡቲ መካከል ያለውን የድንበር አለመግባባት በውይይት ለመፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በመወያየት ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

 

በሙለታ መንገሻ

Dm eri tv subscribe

Eritrean Festival Germany 2019 - ጉጅለ ጽንዓት - Abera Beyene - Wata - Tehambele - Part 3