Dehai News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ወደ ጅቡቲ አቀኑ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Thursday, 06 September 2018

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ወደ ጅቡቲ አቀኑ

አዲስ አበባ፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ወደ ጅቡቲ ማቅናታቸው ተሰማ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለታላቅ አላማ ወደ ጅቡቲ መላካቸው ገልጸዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ወደ ጅቡቲ ያቀኑት ትላንት የተደረገው የሶስትዮሽ ውይይቱን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላም ለማረጋገጥ እንደሚወያዩም ተነግሮዋል፡፡

የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፣ የኤርትራ የውጭ ጉዳ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ኢሴ ናቸው ወደ ጅቡቲ የተጓዙት፡፡

በዚያም ኤርትራ እና ጅቡቲ የድንበር ውዝግብ በሚያሰሙበት ዱሜራ ጉዳይ ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡


Dm eri tv subscribe

ERi-TV, Eritrea: Hamid Idris Awate's story - book released at Festival Eritrea Expo

Hamid idris awate book release

Hdri Media Books on Amazon.com
visit hdrimedia.com