Dehai News

Satenaw.com: ዶ/ር ዐቢይ አህመድና አቶ ደመቀ መኮንን የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Friday, 05 October 2018

ዛሬ ከሰዓት በኃላ በተካሄደው የግንባሩ የአመራርነት የምርጫ ስነ-ስርዓት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የግንባሩ ሊቀመንበር ሆኖ እንዲቀጥሉ ተመርጠዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ ቀጣዩን ድምፅ በማግኘት የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ኢህአዴግን በአመራርነት ለመምራት እጩዎች ሆነው ቀርበው የነበሩት ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከኦዴፓ፣ አቶ ደመቀ መኮንን ከአዴፓ እና ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከህወሓት ናቸው፡፡
ድምፅ በመስጠት 177 ሰው ተሳትፏል፡፡

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከተሰጠው ድምፅ 176 ድምፅ አግኝተዋል፡፡አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ 149 ድምፅ በማግኘት በምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ዶክተር ደብረ ፅዮን ገ/ሚካኤል ለምክትል ሊቀመንበርነት ቀርበው 15 ድምፅ አግኝተዋል፡፡

የደኢህዴን ሊቀመንበር የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በምርጫው አለመሳተፋቸው ተመልክቷል፡፡

ምርጫውን የሚመራ 12 አስመራጭ ኮሚቴ ተሰይሞ የምርጫ ሂደቱ ተከናውኗል፡፡


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events