Dehai News

(ENA) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ሊያነሳ ነው

Posted by: Semere Asmelash

Date: Saturday, 03 November 2018

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ሊያነሳ ነው

አዲስ አበባ - የተባበሩት መንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለማንሳት ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተጠቆመ።

የመንግሥታቱ ድርጅት በኤርትራ ላይ ማዕቀቡን የሚያነሳው አሜሪካ በኤርትራ ላይ ያላትን አቋም መቀየሯን ተከትሎ ነው ተብሏል።

አጃንስ ፍራስ ፕሬስ በምክር ቤቱ የቀረበውን ረቂቅ ሰነድ ጠቅሶ እንደዘገበው ማዕቀቡ ከተነሳ የጦር መሣሪያ ግዥ መፈፀምን ጨምሮ በኤርትራ በከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ተጥሎ የነበረው የጉዞ፣ የኃብት ዝውውር እግዳና ሌሎች ተመሳሳይ ክልከላዎች ይነሳሉ።

የጸጥታው ምክር ቤትም በቀረበው ረቂቅ እቅድ ላይ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም መክሮበት የመጨረሻ ድምጽ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ዲፕሎማቶችም ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር መታረቋን ተከትሎ የአሜሪካ በኤርትራ ላይ ያላትን አቋም ስለቀየረች ረቂቁ ይጸድቃል የሚል ግምት ሰጥተዋል።

ይሁንና አሜሪካ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ ማዕቀቡ ከመነሳቱ በፊት ኤርትራ የሰብዓዊ መብት አያያዟ ማሻሻል አለባት የሚል አቋም ነበራቸው።

ያም ሆኖ አሜሪካ ይህንን አቋሙ እንድትቀይር ያደረጋት የአሜሪካ የደኅንነት አማካሪ ጆን ቦልተን መሆናቸውን አንዳንድ ዲፕሎማቶች ገልጸዋል።

የጸጥታው ምክር ቤት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2009 ኤርትራ በሶማሊያ የመሸገውን አልሸባብ የሽብር ቡድን ትደግፋለች በሚል ነበር ማዕቀብ የተጣለባት።

ይሁንና አሁን በምክር ቤቱ እየተዘዋወረ ያለው ረቂቅ ሰነድ በኤርትራ ላይ የተሟላ መረጃ አለመኖሩን ይጠቅሳል፤ ለመጨረሻ ውሳኔም ለህዳር 14 2018 ዓ.ም ቀን ቀጠሮ ተይዟል።

ኢትዮጵያም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በኩል በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ ለመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ አቅርባለች።

https://www.ena.et/?p=24361#


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events