Dehai News

( የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት) የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያና ኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ድጋፍ ያደርጋል- አምባሳደር ሙርሄድ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Monday, 12 November 2018

የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያና ኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ድጋፍ ያደርጋል- አምባሳደር ሙርሄድ

አዲስአበባ  ህዳር 12/2018 የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያና ኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ሱሳና ሙርሄድ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገሮች ከመንግስታቸው ከፍተኛ የልማት ተጠቃሚ ናት።

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የወረደውን ሰላም እንደሚያደንቁ ገልጸው፤ “በሁለቱ አገሮች ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እንሰራለን” ብለዋል።

አምባሳደር ሱሳና ሙርሄድ እንዳሉት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን አክለዋል።

አምባሳደሯ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እየተወሰዱ ያሉ ሪፎርሞችን እንደሚደግፉም ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪያ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ሰላምን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት ያደነቁት አምባሳደር ሙድሄር “ኢትዮጵያ ሰላምን የማስፈን ስራዎችን እያሻሻለች ትገኛለች፣ በተለይ የዜጎቿን ሰላም ለማስጠበቅ የምታደርገው ነገር ጥሩ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰላምና ጸጥታ ማስልጠኛ ማዕከልን በማጠናከር የእንግሊዝ መንግስት የተሻለ ሰላም አስከባሪዎች እንዲሰለጥኑና በአፍሪካ ቀንድ ሰላም ለማስፈን እንዲችሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

አምባሳደሯ የሁለተኛውን ዓለም ጦርነትን 100ኛ ዓመት በማንሳትና  የጦርነት ጥፋት በመማር አገሮች ያሉትን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፍታት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

“ሁሌም ለሰላም ዘብ መቆም አለብን፣ ሰላም ለማምጣት ትግል ማድረግ አለብን” ብለዋል።

”ሰላምን በዘላቂነት ለማምጣት አሁን ረጅም ጉዞ ይቀረናል ለዚህም ብዙ መስራት አለብን” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

“ባለፉት 100 ዓመታት በዓለም ላይ ሰላምን ለማስፈን አልቻንም፣ አሁን እንደሚመስለኝ ሰላምን ለማስፈን የምናደርገውን ጥረት እጥፍ ማድረግ አለብን” ብለዋል።

ኢትዮጵያና እንግሊዝ ለረጅም ዓመታት በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እና በባህላዊ ጉዳዮች ላይ ግንኙነት አላቸው።

እንግሊዝ ከአፍሪካ አገሮች ውስጥ በመጀመሪያ ኤምባሲዋን የከፈተችው አዲስ አበባ ሲሆን ከአፍሪካ አገሮችም በለንደን ኤምባሲ በመክፈት ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ናት።

የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያና ኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ።


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events