Dehai News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት ዳግም መጀመር የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ሊመሰገኑ ይገባል- ዶ/ር ደብረጽዮን

Posted by: Semere Asmelash

Date: Friday, 11 January 2019

በኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት ዳግም መጀመር የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ሊመሰገኑ ይገባል- ዶ/ር ደብረጽዮን

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2019 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጰያና የኤርትራ ህዝቦች ግንኙነት ዳግም እንዲጀመር ያደረጉ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ምስጋና እንደሚገባቸው የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገለጹ።

የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች በሁመራ ከተማ የህዝብ ለህዝብ መድረክ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል በሺህዎች የሚቆጠሩ የኦምሓጀርን ነዋሪዎች ጨምሮ የሁለቱ ሀገራት የመካላከያ ኃይል አባላት፣ የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንደተናገሩት፥ የተቋረጠው የሀገራቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጀመር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምስጋና ይገባቸዋል።

በኢትዮጵያ የትግራይ ምዕራባዊ ዞንና በኤርትራ ጋሽ ባርካ አጎራባች ህዝቦች ከእንግዲህ የተጀመረውን የሰላም ግንኙነት በማጠናክር ቀጣይ ጉዟቸውን ብሩህ ሊያደርጉ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ለግንኙነቱ ዘላቂነትም የትግራይ ክልላዊ አስፈላጊውን ተግባራት ሁሉ እንደሚያከናውንም አስረድተዋል።

የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ርስቁ አለማው በበኩላችው “የተጀመረ ሰላም ዘላቂ  እንዲሆን  እንሰራለን” ብለዋል።

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱና የአካባቢው ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ነዋሪዎቹ በጋራ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የጋሽ ባርካ ተወካይና የጉልጅ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሓጎስ ዓምደ ብርሃን ”የተጀመረው ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንሰራለን ከንግዲህ ይህን ሰላም እንጠብቀዋለን ማንም አያቋርጠውም” በለዋል።

አራት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተገኙበት ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኘውን የሁመራ-ኦምሓጀርን መንገድ መክፈታቸው ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ መረጃ፦ ከኢዜአ

EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events