Dehai News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) በባህር ዳር ከተማ ሲካሄድ የቆየው 14ኛው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ተጠናቀቀ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Tuesday, 19 March 2019

በባህር ዳር ከተማ ሲካሄድ የቆየው 14ኛው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣(ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባህር ዳር ከተማ ሲካሄድ የነበረው 14ኛው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።

በውድድሩም ኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ ኤርትራ እና ሩዋንዳ 1ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

የውድድሩ የደረጃ ስንጠረዥም፦

1ኛ ኤርትራ፦ በ7 የወርቅ፣ 6 የብር እና 4 የነሃስ ሜዳሊያዎች

2ኛ ኢትዮጵያ፦ በ7 የወርቅ፣ 5 የብር እና 2 የነሃስ ሜዳሊያዎች

3ኛ ሩዋንዳ፦ በ2 የወርቅ፣ 2 የብር እና 3 የነሃስ ሜዳሊያዎች አጠናቀዋል።

ደቡብ አፍሪካ በ1 የወርቅ እና በ3 የነሃስ ሜዳሊያዎች፣ አልጄሪያ በአንድ የብር እና 1 የነሃስ ሜዳሊያዎች እንዲሁም ቡርኪናፋሶ በ2 የነሃስ ሜዳሊያ ከ4ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ለተሳተፉ 16 የአፍሪካ ሀገራትም ልዩ ሽልማት እና የተሳትፎ ምሰከር ወረቀት በመበርከቱ ነው የተገለፀው።

እንዲሁም ውድድር በስኬት እና ሰላማዊ መልኩ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱት የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን እና የፀጥታ ሀይል የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

በናትናኤል ጥጋቡ





7ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 7 - ERi-TV Documentary

Dehai Events