Dehai News

Freedom4Ethiopian.wordPress.com: ወያኔ የመጨረሻውን እርሾ በመጋገር ላይ ነው

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Monday, 06 February 2017

ወያኔ የመጨረሻውን እርሾ በመጋገር ላይ ነው

( መስቀሉ አየለ)

ኢህአዴግ የተባለው የማደንጋሪያ ጭንብል ወልቆ ከወደቆ ሰንብቶዋል። የቀረው ነገር የግዜ ጉዳይ እንደሆነ የገዛ ሰውነቱ ነግሮታል። በየቦታው የሚታየው መተራመስ ሁሉ ሌላ ምክንያት የለውም። በዚህ ሂደት ውስጥ ወያኔ የቀረው አንድ ያልተሞከረ ነገር ቢኖር በራሱ ላይ መፈንቅለ መንግስት አድርጎና ጃኬቱን ቀይሮ በአዲስ መልክ መቅረብ መሆኑን ካሁን በፊት ባቀረብኩት አንድ የዳሰሳ ጥናት ላይ ለመግለጥ ሞክሬ ነበር። ይኽ መላምት እውነት እንደሆነ ከመቸው ግዜ በላይ አሁን ግልጥ ሆኖዋል።

የሃይል አሰላለፉ ምን ይመስላል።
በሶስት አንጃ ተከፍሎ የነበረው የህወሃት የሃይል አሰላለፍ አሁን ወደ ሁለት የወረደ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል።ይኸውም፤

፩ የባለፈውን ሰሞን ህዝባዊ አመጽና አሁን በአመዛኙ ጎንደርና ጎጃምን ያካለለውን ህዝባዊ ተጋድሎ ትከትሎ በአስቸኩዋይ አውጁ ስም ስልጣኑን እያጠናከረ የመጣው በሳሞራ የሚመራው የመከላከያ ሃይልና የወታደራዊ ደህንነቱ ክፍል ነው። አባይ ወልዱና የትግራዩ ሚሊሻ ሙሉ ለሙሉ ለዚሁ አንጃ እጅ የሰጠ ሲሆን ይኽ ሓይል ከግዜ ወደ ግዜ ጡንቻው እየፈረጠመና አድማሱን እያሰፋ መስመሩንም ወደታች እየዘረጋ በመሆኑ ከፖለቲካው አመራር ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መግባቱ በደንብ የተስተዋለ ነገር ነው።

፪ የህወሃት የፖለቲካ ልሂቃን ብለው እራሳቸውን የሰየሙት የነአባይ ጸሃየ ደብረ ጾዮን የመሳሰሉት አከላት ደግሞ ሙሉ ለሙሉ በሙባል ደረጃ አሰላለፋቸውን የሴኪዩሪቲውን ሃይል ከሚዘውረው ከጌታቸው አሰፋ ጋር ያደረጉ ሲሆን የቀድሞዎቹ አፈንጋጮች የተባሉት እና ውስጥ ውስጡን እግራቸውን ለመዘርጋት የማርያም መንገድ ሲፈልጉ የኖሩት እነ ጻድቃን፣ ሰዬ አብራሃ፣ ስብሃትና አበበ ተክለሃይማኖት የመሳሰሉትም ከዚሁ ከጌታቸው አሰፋ ጋር መጠለያ ማግኘታው ሲታወቅ ይህ ቡድን በዋናነት የውጭ መንግስታት በተለይም የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግስታትን የፖለቲካ ድጋፍ ያገኘ ነው።

በጥቅሉ ይኽ ለሁለት የተከፈለው የህወሃት አሰላለፍ መሃላቸውን ያለውን ልዩነት ለማጠብብ የሚያስችል አማካኝ መንገድ ሊገኝ ስላልቻለ ቅራኔው ከግዜ ወደ ግዜ እየሰፋና ሊታረቅ ወደ ማይችልበት ቀውስ ውስጥ እያመራ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ችግሩ ወዲህ ነው። እነዚህ ሁለት አካላት ያላባቸው ቅራኔ ሊፈታ እንደ ማይችል ግልጽ በሆነበት በዚህ ሰዓት የሳሞራ አንጃ በኮማንድ ፖስቱ ሽፋን መዋቅሩን ወደታች ለመዘርጋት የሚያደርገው ሙከራ የፖለቲካውንና የደህንነቱን መዋቅር ሙሉ በሙሉ በማንሳፈፍ ለመፈንቅለ መንግስት እያመቻቻቸው እንደሆነ እራሳቸው እነ አባይ ጸሃይ አያጡትም። ነገር ግን መፈንቅለ መንግስቱ ቢካሄድ በቀጣዩ ምን ሊከስት ይችላል የሚለውን ነገር ግን ከግምት በላይ መሄድ ይቻላል።

ይኽውም መፈንቅለ መንግስት ለማካሄድ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ማእከላዊነት ያለው (በአንድ ኮማንድ ሴንተር የሚመራ) አንጻራዊ በሆነ መልኩ ተቁዋማዊ ቅርጽ ያለው የወታደራዊ እና የፖለቲካ አድርጃጀት ሊኖር ግድ ይላል። ነገር ግን ዘረኝት እንደጋንግሪን ውስጥ ውስጡን በልቶ የጨረሰውና በዘረፋ ቅሌት በስብሶ እርስ በራሱ ለመበላላት ተፋጦ የቆመ ሃይል ባለበት፣ አገሪቱን ለመምራት ይጥቀምበት የነበረው የዘር ፖለቲካ ውልቅልቁ ወጥቶ ህዝባዊ ማእበሉ እንደ አሬራ ሊንጠው በተቃረበበት ፣ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሃይል አሰላለፍ መልኩን ቀይሮ ከሰሜን ሶማሊያ እስከ ደቡብ ሱዳን የግብጽ ወታደራዊ ሃይል መሰረት እየጣለ በመጣበት ሰዓት፣ እስከ ዛሬ ድረስ ተንጠልጥሎ የቆየባቸው አሜሪካና እንድሊዝ በትራምፕ ወደ ስልጣን መውጣትና የእንግሊዝን ከአውሮፓ ህብረት መውጣት የራሳቸውን ፖለቲካ መስቀለኛ መንገድ ላይ በቆመበት ሰዓት የሚካሄድ መፈንቅለ መንግስት የትግራዩ ገዥ ጉጅሌ መጨረሻው እንደ ዳይኖስረስ እራሱን በራሱ እንዲበላ በር ከመክፈት ውጭ ሌላ ፋይዳ የለውም። በጣም አስገራሚው ነገር ግን ይኽም ሁሉ ችግር እያለ ወያኔ ግን ከውጩ ይልቅ የውስጥ ቅራኔውን ማስታረቅ የሚችልበት ግዜም, ጉልበትም, ጥበብም, አደረጃጀትም ስለሌለው ይኽን በደም ጎርፍ የሚጠናቀቅ መፈንቅለ መንግስት ላለማድረግ መብትም አቅምም የለውም።

14088937_624973021001365_1677821973_n


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events