Date: Thursday, 09 November 2017
እነ አላሙዲ በሳዑዲ “ቂሊንጦ”
November 9, 2017 09:44 pm By Editor 3 Comments
ቅዳሜ ማታ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የሳዑዲ ልዑላንና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም አላሙዲ መሬት ላይ ተኝተው የሚያሳይ ፎቶ ዴይሊ ሜይል በድረገጹ ላይ ለቋል። “ቂሊንጦ” በሚሰኝ ሁኔታ “አገልግሎት”
እየተሰጣቸው እንደሆነ ከዴይሊ ሜይል ዘገባ ለመረዳት ይቻላል።
“ከሳዑዲ መንግሥት ምንጮች የተገኘ” በማለት ዴይሊ ሜይል የለቀቀው ይህ ፎቶ እንደሚያሳየው አይነኬዎቹ እነ ልዑል አልዋሊድ (የእኛን ጉድ አላሙዲንን ጨምሮ) በሥሥ ፍራሽ ላይ ሪትዝ ካርልተን ሆቴል መሬት ላይ ተኝተው ይታያል። ጋዜጣው ሲያላግጥም “የሳዑዲ ልዑላን ባለ አምስት ኮከብ እስርቤት ውስጥ” በማለት ለዘገባው ርዕስ ሰጥቶታል። ጋዜጣው ሁኔታውን “የሚያሳፍር” በማለት የጠቀሰው ሲሆን በትንሽ ብርድልብስ ተጠቅልለው ለዚህ ውርደት መብቃታቸው ቢፈቱ እንኳን ውርደቱን ተቀብለው ለመኖር የሚያቅታቸው እንደሆነ አስተያየት ተሰጥቶበታል።
ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆዩ ባይታወቅም ምርመራው እየተካሄደ በዚህ መልኩ ለሳምንታት ሊቆዩ ይችላሉ የሚል ግምት ይሰጣል። (የጋዜጣው ሙሉ መረጃ እዚህ ላይ ይገኛል)
ሰኞ ዕለት የሳዑዲ መንግሥት እንዳስታወቀው የግለሰቦቹ የባንክ ሒሳብ እንዳይንቀሳቀስ ይደረጋል፤ ሃብታቸውም የሳዑዲ መንግሥት ንብረት ይሆናል በማለት መግለጫ ሰጥቷል።
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ
ደላላው “ባለሃብት” አል-አሙዲ በቁጥጥር ሥር ውሏል!
የሳዑዲ የዙፋን ተስፈኛ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን 11 ልዑላንን እና 38 የመንግሥት ባለሥልጣናትን (የቀድሞውን ጨምሮ) እንዲሁም የንግድ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ። ደላላ (ተጠሪ ወይም front man) ባለሃብት እንደሆነ የሚነገርለት በግማሽ ኢትዮጵያዊ የሆነው ሞሐመድ አላሙዲ (አል-አሙዲ) በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል መሆኑን ጎልጉል አረጋግጧል። ንጉሥ ሳልማን የሕዝብን ንብረት የመዘበረ ማንም ሰው ተጠያቂ ይሆናል፤ “ማንንም አንፈራም” ብለዋል። ዜናው የተወሳሰበ ትስስር ያላቸውን የአላሙዲ “ወዳጆች” ከፍተኛ ሥጋት ላይ ጥሏል።.................
ማንበቡ ታች ቀጥል።