World News

Goolgule.com: በኢትዮጵያ የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው ወታደራዊ አገዛዝ ሊታወጅ ነው!

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Friday, 16 February 2018

በኢትዮጵያ የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው ወታደራዊ አገዛዝ ሊታወጅ ነው!

 

በኢትዮጵያ በተከታታይ የዘለቀውን ሕዝባዊ ተቃውሞ መቆጣጠር የተሳነው ህወሓት በኢትዮጵያ በአስቸኳይ አዋጅ ስም አገሪቷን በወታደራዊ አስተዳደር ስር ለማስተዳደር ኣዋጅ አንደሚያወጣ ተሰማ። የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው አዋጅ ምናልባትም ዛሬ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

  • ያለፈው የኢህአዴግ ስብሰባ ወቅት ስምምነት ተደርሶበት የነበረው ሁሉንም ያሳተፈ የሽግግር መንግስት ምስረታ ህወሓት ኣልቀበለውም ብሏል፥
  • ይህንን ተከትሎ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣኑ እንዲወርድ በህወሓት ግፊት ሲደረግበት ቆይቷል፤
  • የሃይለማርያም በፈቃዱ ከስልጣን መውረድ ለህወሓት የደኢህዴንን ስጋት እንዲቀንስለት ታስቦ የተደረገ ግፊት ነው፥
  • የኦህዴድ መክዳትና የብአዴን መከተል ላይ ደኢህዴን ከተጨመረ የህወሓትን ህልውና አደጋ ላይ መጣሉ ስላሰጋው ነው ህወሓት ሃይለማርያም በፈቃዱ ለቀቀ ማስባል የፈለገው፥
  • ወታደራዊ አገዛዝ ከታወጀ በኋላ ህወሓት ያለ ርህራሄ ማንኛውንም ተቃውሞ “የመጨረሻ ውሳኔ” በማስተላለፍ ታይቶ የማይታወቅ ደም ማፋሰስ በአገሪታ ላይ በማስከተል ስልጣኑን ለማረጋጋት የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል፤
  • ይህንን ተፈጻሚ ለማድረግና ከጌቶቹ ፈቃድ ለማግኘት በኦሮሞ ስም ለትግራይ የሚጫወተው ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ/ወልደጻድቅ አሜሪካ ይገኛል፥
  • ጎልጉል የደረሰው መረጃ አንደሚያመለክተው በአሜሪካኖቹ በኩል ሙሉ ስምምነት ባይኖርም  አንዳንዶቹ ግን “የአሜሪካንን ጥቅም የሚያስጠብቁት ትግሬዎች ናቸው” በማለት ለህወሓት ሙሉ ስልጣን እንዲሰጠው በግልጽ ይናገራሉ፤
  • ከዚህ ጋር በተያያዘ ወታደራዊው አገዛዝ ዛሬ ሲታወጅ የአሜሪካ ድጋፍ ወደ ህወሓት ማዘመሙን በግልጽ የሚያሳይ ይሆናል፥
  • በግብጽ የፕሬዚዳንት ሙርሲን አስተዳደር አውርዶ የአሜሪካ ወኪል በሆነው አልሲሲ ለመተካት በተደረገው ተቃውሞ አደባባይ የወጡ ተቃዋሚ ዜጎችን የአልሲሲ ኃይል ሲጨፈጭፍ ምዕራባውያን በተለይም አሜሪካ የውስጥ ድጋፏን እንደሰጠችው በኢትዮጵያም በቀጣይ የሚከሰተው ይህ እንደሚሆን ጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል
  • የኃይል አገዛዝ የትኛውንም መንግሥት እንዳላጸናው ከታሪክ የማይማረው ህወሓት አሁንም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የበቀል ርምጃውንም ለመውሰድ ሰይፉን ስሏል፥ የጌቶቹን ቡራኬም እየተቀበለ ነው።

(ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናትማለን)


6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events