World News

Satenaw.com: ጣእሩ የበዛው የቀን ጅብ!

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Monday, 09 July 2018

(መስቀሉ አየለ)

በተለምዶ እንደምናውቀው ሁለት እራሳቸውን የቻሉ ጎረቤታም አገሮች በመካከላቸው እንዳለው ግንኙነት በሰላም ሲኖሩም ሆነ ያላቸው ጉርብትና ችግር ውስጥ ሲገባ ለውስጡም ለውጩም ግልጽ የሆነ የሚታይ መስመር አለ። የእኛና የኤርትራ ግንኙነት ግን ከዚህ በእጅጉ ያፈነገጠ ነው። ውስብስብ የሚያደርገውም ይኼው የማይካድ ሃቅ ነው። አስመራና አዲስ አበባ ሆነው መገናኘት ያልቻሉ ከአንድ ቤተሰብ የተከፈሉ ቁጥራቸው በ 10 ሽዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች መኖራቸው በእርግጥ የሁለቱ አገሮች እጣ ፋንታም ሆነ አብሮነት ከላይ እንደሚታየው የተያያዘ መሆኑን መካድ አይቻልም።

ሻቢያ በበኩሉ ከቀን አንድ ጀምሮ “እኔ ችግሬ የትግራይ ጉጅሌ ብቻ ነው፤ እርሱ ጋር ደግሞ ተያይዘን እንጦርጦስ እንወርዳታለን እንጂ ከሰማይ በታች በምንም ነገር እርቅ ብሎ ነገር አይታሰብም” በሚለው አቋሙ ጸንቶ ይህንን ቀን ሲጠብቅ ብዙ መራራ አመታቶችን ታግሷል።

ሻቢያ አሁንም እንደገና ያስተላለፈው አቋም ይህንኑ ነው።ነጮቹ ጭምር እንዲያውቁት በእንግሊዝኛ ሳይቀር የተናገረው ” ከቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆኘ ወያኔ የተባለውን ደራጎን አንገቱን እቆርጣለሁ” የሚል ነው።በሌላ በኩል የወያኔ የጡት አባት ሆነው የኖሩት የምእራብ አገራት መንግስታት ሻቢያን የምስራቅ አፍሪካው አተራማሽ ሃይል አድርገው በመውሰድ ከአንገት ቆራጩ አይሲስ ጋር ሲደመሩትና ዲፕሎማቶቹን ባለማቀፍ መድረክ ፊት እንደ ውሻ ሲያንከላፍቷቸው እንዳኖልሩ ገዜ መልካም ነውና ዛሬ የቀን ጅቦቹ ለእሩብ ክፍለ ዘመን ከሻገቱበት የሚኒሊክ ቤተመንግስት ተነቅለው ወደ ጉሯቸው መመለስ ሲጀመሩ የሰላም አየሩ ከኢትዮጵያም ባሻገር በቀናት ውስጥ የአፍሪካ ቀንድን ሁሉ ማዳረስ መጀመሩ በርግጥም እስከ ዛሬ ድረስ እውነተኛው የችግሩ ጠንቅ ማን እንደነበር አረጋግጧል።

ከቀን ወደ ቀን በከፍተኛ ፍጥነት እየተደረመሰ የመጣው የጉጅሌው የሽፍታ ኤምፓየር ሊቀመንበር ደብረ ሌጊዮን ደግሞ እመራዋለሁ የሚለው ድርጅትና ወገን እጣ ፋንታ ምን እየሆነ እንደሆነ ስርዓት ባለው መልኩ እንደመተንተን “እኛ ብቻ አይደለንም የቀንጅቦች፤ እነ እንትናም ድርጅት ውስጥ የቀን ጅቦች አሉ” የሚል እሰጣ እገባ ሲገባ ላየን ሰዎች ነገሩ የቱን ያህል ያለቀለት መሆኑ ነው የገባን። ሲጀመር፤ ምንም እንኳን ይሄ ቃል የተነገረው በጠሚሩ አንደበት ቢሆንም ደብረ ሌጊዮኑ ግን የቀን ጅብነቱን አምኖ ላለመቀብል ቅንጣት ታክል ሳያንገራግር ባንድ ግዜ ወርዶ “እነ እከሌም የቀን ጅብ ናቸው” አይነት ክርክር ውስጥ ሲገባ የአቅሙን ልክ ፍንትው አድርጎ አሳይቷል። በእርግጥ ወትሮም የነሱ ደረጃ በእንዲህ አይነት የመንደርተኛ ወሬ ክርክር ጉንጭ ማልፋት እንጅ መንግስት ሆኖ ፖሊሲ መንተንኑ የተቀቡበትም የሰለጠኑበትም እንዳልሆነ ቀድሞውኑ እናውቀዋለን።

ከዚያ በተረፈ አብዮቱ “ከመከላከል ወደ ማጥቃት” ከተሸጋገረ ግዜ ጀምሮ ከቀን ጅቦቹም ሆነ ከቀድሞው የብአዴን ዞምቢዎች ወጥቶ ትንፍሽ የሚል ሰው መጥፋቱ ሌላው የሰሞኑ ትእይንት ሲሆን ደቂቀ መለሳውያን እንደ “ሙሴ” ሲያዩት የነበረው አባይ ጸሃየ የሚባል የሌብነት ሚኒስትር ደግሞ በበኩሉ የሚያደርገው ቢያጣ፣ የሚያቀርበውም ቢያጣ ሰሎሞን ተካልኝ ከተባለ ሆዱ ጭንቅላት የሆነለት ዘለፈቶ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ “ልክ አስገቢው” ምን ያህል ልክ እንደገባ ያሳየ ክስተት ነበር ማለት ይቻላል።

ለማጠቃለል፤
በተለይም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በመሃል አገር የተጀመረው ጸረ ወያኔ ትግል በነፍጥ መታገዝ ሲጀምር ከሌለ ትንታኔ ተነስተው ትግራይን ከደጋማው “የኤርትራ ህዝብ ጋር አንድ የሚያደርግ ማህበረ አጋዚያን” የሚባል ንቅናቄ መፍጠራቸውንና እስራኤልን ጨምሮ ይህንን ጅማሮ በበጎ የሚያዩት በርካታ መንግስታት መኖራቸውን እየጠቀሱ ሲያሽካኩብን የነበሩት የቀን ጅቦቹ ግልገሎች ማን ለማን እንደሚቀርብ በዛሬው እለት ያዩና እርማቸውን ያወጡ ይመስለኛል።ከዚህ በተረፈ ዛሬ በ አስመራ የታየውን አብሮነት ስጋና ደም ለብሶ ወደ ፍሬ ክብር እንዳይበቃ የቀን ጅቡ የማይፈነቅለው ዲንጋይ እንደማይኖር የሚጠበቅ ሲሆን ነገር ግን መከራ ሞቱን ከመጋፈጥ ውጭ ከመሆን የሚቀር ነገር እንደማይኖር ግልጽ ነው። ጉድጓዱን ስትቆፍር አርቀህ አትቆፍር የሚገባበት አይታወቅምና ተብሎ እንደተተረተው ሁሉ።


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events