World News

EthioThinkThank.com:1. ዶላር ወደ ውጪ፣ ጦር መሳሪያ ወደ ውስጥ! 2. ወደ ትግራይ ክልል በሽፍን መኪና ሲጓጓዝ የነበረ ስድስት ኩንታል ብር ባቲ ከተማ ላይ ተያዘ፡፡

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Monday, 23 July 2018

News

ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከብሄራዊ መረጃና ደህነት፣ ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር ሆኖ ህብርተሰቡን ማዕከል ባደረገ መልኩ በተከሄደው የጥቂት ቀናት ዘመቻ ገንዘቡ ከአገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ጥቂት ቀናት በጥናት ላይ በተካሄደው ዘመቻ ከ1ሺህ በላይ የነፍስ ወከፍና የቡድን ጦር መሳሪያ እንዲሁም 80 ሺህ የሽጉጥና ክላሽ ጥይቶች ወደ አገር ሊገቡ ሲል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

ከገንዘቡ በተጨማሪ በህገ ወጥ ድርጊቱ ላይ የተሳፉ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገባቸው መሆኑንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአገር ሊወጣ ሲል፣ የጦር መሳሪያው ደግሞ ወደ አገር ሊገባ ሲል መያዙ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጫና ለመፍጠርና አገራዊ አለመረጋጋትን ለመፍጠር የተቀናጀ ስራ መኖሩን ተገንዝቦ ፖሊስ ጥልቅ ምርመራ እያረገ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ሪፖርተር፡ ጥላሁን ካሳ

ምንጭ፦ EBC

***********************************************************

ወደ ትግራይ ክልል በሽፍን መኪና ሲጓጓዝ የነበረ ስድስት ኩንታል ብር ባቲ ከተማ ላይ ተያዘ፡፡

ወደ ትግራይ ክልል በሽፍን መኪና ሲጓጓዝ የነበረ ስድስት (6) ኩንታል_ብር ባቲ ከተማ ላይ ተያዘ፡፡ ከአንድ የባቲ ከተማ ነዋሪ ጋር ስለ ጉዳዩ በስልክ ተወያይተናል፡፡

Listen:

https://mereja.com/amharic/v2/36031

 

6ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 6 - ERi-TV Documentary

Dehai Events