አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም በኢትዮጵያ በቆይታቸው ለዚህ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው እምነታቸውን ገልጸዋል።
ዶክተር ወርቅነህ አክለውም፥ በድንበር ንግድና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ የተደረገው ያላሰለሰ ጥረት ወደሚፈለገው አቅጣጫ እያመራ መሆኑ እንዳስደሰታቸውም ዶክተር ወርቅነህ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ስታደርግ የቆየችውን ከፍተኛ ጥረት እሰከፍጻሜው አጠናክራ እንደምትቀጥል አስረድተዋል።
የኤርትራው አምባሳደር በበኩላቸው፥ በቆይታቸው የሁለቱን አገሮች ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።