World News

( መረጃ ) የህወሃቶች መርዶ!

Posted by: Semere Asmelash

Date: Friday, 09 November 2018

የህወሃቶች መርዶ!



ህወሃት ሌትና ቀን ማሥኖ የሃገሪቱን ገንዘብ ለዓለም ሎቢሥቶች ከፍሎ በኤርትራ ላይ ያሥጣለው ማዕቀብ በቅርቡ ሊነሳ ነው።

የህወሃቶች መርዶ!

ህወሃት ሌትና ቀን ማሥኖ የሃገሪቱን ገንዘብ ለዓለም ሎቢሥቶች ከፍሎ በኤርትራ ላይ ያሥጣለው ማዕቀብ በቅርቡ ሊነሳ ነው።

ከምንም በላይ ህወሃቶች አቅላቸውን ጥለው በንዴት የሚያብዱና የሚሰክሩበት፡ ማዕቅ ለብሰው አመድ ነሥንሰው የሚያዝኑበት፡ ልባቸው እርር ድብን የሚልበት ጊዜ ቢኖር ይሄ በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የተነሳ ዕለት ነው።

እውነቱን ለመናገር ኤርትራውያንን ለሥደትና ለሥራ አጥነት አሳልፎ የሰጠው ታላቁ ሚስጥር ይሄ በህወሃት አሻጥርና ተንኮል የተጣለ ማዕቀብ ነበር።

በኤርትራና ኤርትራውያን ላይ የደረሰው ማዕቀብ፡ የኤርትራውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ሃብት ንብረታቸው በህወሃት የመዘረፍ፡ የኤርትራውያን ከኤትዮጵያ በኃይል የመባረራቸው፡ በባድመ ሰበብ በጦርነት ማለቃቸው፡ በጦርነት ስጋት ውስጥ የመኖራቸው ምክንያት ህወሃትና ህወሃት ብቻ ነበር።ህወሃት ትላንት ለአማራ ህዝብና ለኤርትራውያን የሰቆቃና የመከራ ዘመን እንዲያሳልፉ ተንኮል ሲሰራ የኖረ ዛሬና ነገ ደግሞ በዘር ትግሬ ለሆነው የትግራይ ህዝብ ተዝቆና ተክፍሎ የማያልቅ ዕዳ ውስጥ የሚያስገባ ደባ እየሰራ ነው።

በዘር ትግሬ በሆነው የትግራይ ህዝብ እየማለና እየተገዘተ የአፋርን ህዝብ ደም በግፍ የሚያፈሰው ህወሃት፡ የሶማሌና ኦሮሞ ወገኖቻችንን ደም ታፈሰሰው ህወሃት፡ የሴራ እሳት እየቆሰቆሰ የሲዳማና ወላይታ፡ የጉራጌና ከፋ፡ የአኙዋክና የሱርማን ህዝብ ደም ያፈሰሰው ህወሃት በዘር ትግሬ የሆነውን የትግራይን ህዝብ የጥቁር ደም ባለዳ እንዲሆን አድርጎታል።

አሁንም የትግራይ ህዝብ በህወሃት ላይ ጠንካራ ዘመቻ ካልከፈተና እራሱን የሚወክል ከጥቁር ደም የጸዳ ሃቀኛ ድርጅት ካልመሰረተ ወደ ግብዝበት የተቀየረው ህወሃት የሚያመጣው ዕዳና መዘዝ የከፋ ነው።







EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events