Date: Wednesday, 21 November 2018
የግንባሩ ሰራዊት ዛሬ ከአስመራ ተነስተው ጅግጅጋ ከተማ ሲገቡም የክልሉ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ደጋፊዎቻቸው አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከግንባሩ የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ግንባሩ የዛሬ ወር በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ የሚታወስ ነው።
በወቅቱ በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራ ልዑክ ወደ ኤርትራ በማምራት ከቡድኑ ጋር ባደረገው ድርድር ስምምነት ተደርሷል።
በዚህም ለረጅም አመታት የትጥቅ ትግልን አማራጭ አድርጎ ሲንቀሳቀስ የቆየው ግንባሩ፥ ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ስምምነት ላይ መድረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልፀው ነበር።
የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር ከስምምነቱ ቀደም ብሎ ልዑኩን ወደ ሀገር መላኩም ይታወሳል።