World News

(ዶይቸ ቬለ) በግድያ የተጠረጠረዉ ኤርትራዊ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Tuesday, 30 July 2019

አፍሪቃ ቀን 30.07.2019  ቁልፍ ቃላት ኤርትራዊ, ግድያ, ፍራንክፈርት

በግድያ የተጠረጠረዉ ኤርትራዊ


ኤርትራዊዉ ፍራንክፈርት ባቡር ጣቢያ የነበሩ እናት ልጅን በፍጥነት በሚጓዝ ባቡር ፊት ገፍትሮ ጥሏቸዋል።እናትየዋ ከባቡሩ ሐዲድ ተንከባላ ስታመልጥ የስምት ዓመቱ ሕፃን ግን እዚያዉ ሞቷል።ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ኤርትራዊዉ ሌላ ሴትዮ ወደ ሐዲዱ ለመገፍተር ሞክሮ አልተሳከለትም

Deutschland Attacke im Frankfurter Hauptbahnhof (Imago Images/epd/H. Lyding)

ፍራንክፈርት-ጀርመን ዉስጥ የ8ዓመት ሕፃንን ትናንት በባቡር አስድጦ በማስገደል ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘዉ ኤርትራዊ፣ ሲዊትዘርላንድ ዉስጥ በፖሊስ የሚፈለግ እንደነበር የጀርመን ፖሊስ አስታወቀ።የጀርመን የፌደራል ፖሊስ አዛዥ ዲተር ሮማን ዛሬ እንዳስታወቁት ሰዉዬዉ ሲዊዘርላንድ ዉስጥ አንዲት ጎረቤቱን በጩቤ ለመዉጋት በማስፈራራት ወንጀል ሲታደን ነበር።የአቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ ናድያ ኒሰን እንደሚሉት ደግሞ የአርባ ዓመቱ ጎልማሳ  እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2006 ጀምሮ ባዝል-ሲዊትዘርላንድ ዉስጥ የሚኖር ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነዉ።«አቃቤ ሕግ የግድያና ድርብ የግድያ ሙከራ ክስ ለመመስረት እየተዘጋጀ ነዉ።ስለዚሕ የእስራት ዋራንት ይጠይቃል።በደረሰን መረጃ መሠረት ሰዉዬዉ አርባ ዓመቱ ነዉ።ኤርትራ የተወለደና የኤርትራ ዜጋ ነዉ።ከ2006 ጀምሮ ሲዊትዘርላንድ ዉስጥ እንደኖረ፣ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት እንደሆነም ተነግሯል።»

Nach Attacke im Frankfurter Hauptbahnhof (picture-alliance/dpa/F. Rumpenhorst)

ኤርትራዊዉ ፍራንክፈርት ባቡር ጣቢያ የነበሩ እናት ልጅን በፍጥነት በሚጓዝ ባቡር ፊት ገፍትሮ ጥሏቸዋል።እናትየዋ ከባቡሩ ሐዲድ ተንከባላ ስታመልጥ የስምት ዓመቱ ሕፃን ግን እዚያዉ ሞቷል።ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ኤርትራዊዉ ሌላ ሴትዮ ወደ ሐዲዱ ለመገፍተር ሞክሮ አልተሳከለትም።አደጋዉን ካደረሰ በኋላ ለማምለጥ ሲሮጥ ባካባቢዉ በነበረዉ ሕዝብና እርፍት ላይ በነበረ ፖሊስ ርብርብ ተይዟል።ፖሊስ እንደሚገምተዉ ሰዉዬዉ አቅሉን ሳይስት አይቀርም።የጀርመን የሐገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሆረስት ዜሆፈርን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ የፌደራልና ግድያዉ የተፈፀመበት የሔሰን ግዛት ባለስልጣናት እረፍታቸዉን አቋርጠዉ የግድያዉን ምክንያትና የገዳዩን ማንነት እያጣሩ ነዉ።
ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ


7ይ ክፋል: ማዕበል ስርሒት ፈንቅል - የካቲት 1990 - ሰነዳዊት ፊልም| sirihit fenkil 1990 - part 7 - ERi-TV Documentary

Dehai Events