Basic

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅና ጠ/ሚ ዐቢይ ከፕሬዚደንት ኢሳያስ ጋር ተገናኙ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Monday, 04 May 2020

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅና ጠ/ሚ ዐቢይ ከፕሬዚደንት ኢሳያስ ጋር ተገናኙ

አዲስ አበባ፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከኤርትራው ከፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጣት መረጃ “ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በድጋሚ መጡ ለማለት እወዳለሁ” ብለዋል።

“ለሁለት ቀናት በሚያደርጉት ቆይታ፣ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እናደርጋለን፤ የዓለም አቀፋ ማኅበረሰብ አካል በመሆናችን ስለ ተጋፈጥናቸው ፈታኝ ሁኔታዎች እንወያይባቸዋለን” ሲሉም ገልፀዋል።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው እለት ነው አዲስ አበባ የገቡት።
 


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events