Dehai News

Satenaw.com: የጀኔራሎቹ ጻድቃን እና አበበ ነገር!

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Wednesday, 14 June 2017

የጀኔራሎቹ ጻድቃን እና አበበ ነገር!

አለበል አማረ

Posted on June 14, 2017

https://i0.wp.com/www.satenaw.com/amharic/wp-content/uploads/2017/06/Tsadikan-and-ababe-1024x424.jpg?resize=550%2C228 ሁለቱም የህወሃት የጦር አለቆች ገና ከበረሃ ትግል ጀምረው የጠበቀ ጓደኝነት የነበራቸው፥ የኮ/ መንግስቱ ስርዓት ከፈረሰ በኋላም የመከላከያ ሃብትና የሰው ሃይል በእጃቸው የወደቀላቸው ጻድቃን የምድር ሃይሉ ላይ ነገሰ፥ አበበም አየር ሃይሉን የግል ካምፓኒው አደረገው። ድንገት የፈነዳው የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት የሁለቱን ጀኔራሎች ቀጣይ ሂወት የደላና የተቀማጠለ እንደሚያደርገው ተገመተ። ለጦርነቱ ማስፈጸሚያ እንዲውል የተመደበው ብርና ዶላር በእጃቸው ገባ፥ ከስራው ከባድ ሚስጥራዊነት የተነሳ ለጦርነቱ የሚያስፈልጉ አልባሳትን፣ መሳሪያን፣ ምግብን፣ጥይትንና ተሽከርካሪን እና ሌሎችንም ያለ ጨረታና ያለ የግዥ መመሪያ በሁለቱ ጀኔራሎች ውሳኔ ብቻ እንዲገዛ ተደረገ። ከሰውየው በስተቀር የኢሀዴግ ስራ አመራር እንኳን የማወቅ እድል አልነበራቸውም። እናማ የድሃ ልጅ በየግንባሩ እየረገፈ እነሱ ስለዘረፉት ሃብት ነበር የሚያስቡት፥ በዚያ አጭር የሁለት አመት ጦርነት 97 ሽህ በላይ ወጣት ሂወት የተቀጠፈው 170 ሽህ በላይ ወጣት ለአካል ጉዳት የተዳረገው ጦሩን እንዲያዋጉ የተመደቡት ጻድቃንና አበበ ስለ ጦርነት ሳይሆን የሚያስቡት ስለገንዘብ ስለነበረ ነው። ከጦርነቱ በኋላም የጦርነቱን ትራፊ ሃብትና በሰላም ማስከበር ይገኝ የነበረው የውጭ ገቢ የጻድቃንና የአበባ የግል ባጀት ነበር።

1994 ላይ ተፈጥሮ በነበረው የሌቦች ክፍፍልና አለመግባባት ለጻድቃንና አበበ ከባድ ፈተና ነበር፥ በወቅቱ የበላይነት የነበራቸው የነ ተወልደ ወልደማሪያም ቡድን ስለነበረ ጀኔራሎቹም ከነ ተወልደ መጠጋት አማራጭ አድርገውት ነበር። ሟቹ ሁኔታወችን በማስተካከል ላይ እያለ ሳያስቡት ከስልጣን አወረዳቸው። ቀኑን ለጊዜው ባላስታውሰውም ሁለቱም /ሎች ከአበበ ቤት እንደተቀመጡ ከስልጣን ተወግደው ጡረታ የወጡበትን የመለስ ፊርማ ያለበትን ደብዳቤ ወስደን ሰጥተን በታዘዝነው መሰረት አጃቢወቻቸውንና መኪኖቻቸውን ይዘን ሄድን /እኔም የነበርኩበትን ለመግለጽ ነው።

ሰወቹ በዚህ ሁኔታ ከተወገዱ በኋላ ቀጣይ ይታሰራሉ ብለን ሁላችንም እንጠብቅ ነበር። የሆነው ግን ሌላ ነው፥ ጻድቃን በመለስ እውቅናና ድጋፍ በተባበሩት መንግስታት የሱዳን የጸጥታ ክትትልና የአፍሪካ የግጭት ጥናት ተደርጎ ተሾመ። የተገኘውን አጋጣሚ ተጠቅሞ በደቡብ ሱዳን ኢኮኖሚ ላይም ትግሬወችን በደንብ አድርጎ ተከለ። ሁለቱንም ጀኔራሎች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እስከ አሜሪካ ያሉ የትምህርት እድሎች ወለል ብለው ተከፈቱላቸው። ዛሬ ሁለቱም ጀኔራሎች ትላልቅ የኢኮኖሚ ተቋሞች ላይ ባለ አክሲዮን ናቸው።

መለስ ዜናዊ፥ እነዚህ ጀኔራሎች ስልጣኑን ሊነጥቁት ከነበሩ ሰወች ጋር ማበራቸውን እያወቀ የእሱ ዘሮች ስለሆኑ ሊጨክንባቸው አልፈለገም። / ሃይሌ ጥላሁን የሚባል አማራ ነበር። ከነ / ተፈራ ማሞ ጋር ተመሳጥረህ ይሆናል በሚል ጥርጣሬ ብቻ ያለምንም ጡረታ ተባረረ። ሃይሌ ከሌሎቹ የተሻለና ሁለት የማስትሬት ድግሪ ያለው ስለነበረ ባህርዳር NGO ተቀጥሮ ወር ሳይሞለው እንዲባረር አደረጉት፡ መጨረሻም ተንከራትቶ ተንከራትቶ ሞተላቸው።

እናም ለማለት የፈለኩት፥ / ጻድቃንም ሆነ / አበበ የወያኔ ኢህአዲግን እድሜ ለማርዘም አሁን ስልጣን ላይ ካሉት ወያኔወች በላይ ይደክማሉ ይሮጣሉ።

 


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events