Dehai News

Zehabesha.com: አስራ ሁለቱ የአባይ ጸሃዬ ልጆች ወደ ውጭ ሃገር እንዲወጡ ተደረገ

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Thursday, 07 September 2017

አስራ ሁለቱ የአባይ ጸሃዬ ልጆች ወደ ውጭ ሃገር እንዲወጡ ተደረገ

Listen:

https://www.youtube.com/embed/m5uaAu_3wv0?vq=highres

በሙስና ወንጀል ውስጥ እጃቸው አለበት የሚነገረው አቶ አባይ ጸሃዬ ልጆቹን በሙሉ ወደ ውጭ እንዲሸሹ ማድረጉን ከታማኝ ምንጮች የተገኘ መረጃ ለማረጋገጥ ችለናል።

የውጩን ንግድ በሞኖፖል ይዘውት የነበሩት የአባይ ልጆች በአሁን ሰዓት በአሜሪካን ሃገር ውስጥ ናቸው።

የአስራ ሁለት ልጆች አባት የሆነው አቶ አባይ ጸሃዬ ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን 77 ቢሊየን ብር በማባከን የሚጠቀስ ሙሰኛ ቢሆንም እስካሁን ተይዞ ሊጠየቅ ግን አልቻለም። አቶ አባይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በፌደራል ጉዳዮች እና በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ በሃላፊነት ሲሰራ የዘረፈውን ገንዘብ በልጆቹ ስም ንግድ ላይ ማዋሉንም የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

ከአባይ ጸሃዬ ልጆች ውስጥ ቤቢ የተባለችው ልጁ በአዲስ አበባ ብቻ 7 ሕንጻዎች ያላት ሲሆን፤ በዱባይ እና በአሜሪካም ትላልቅ ህንጻዎች እና የንግድ ተቋማት እንዳላት ምንጮቹ ገልጸዋል። ጤፍ፣ በርበሬ፤ እንጀራ ወደ አውሮፓ እና ሰሜን አመሪካ የሚላኩ የእርሻ እና የባልትና ውጤቶች በሙሉ የተያዙት በአባይ ጸሃይ ልጆች መሆኑንም ካገኘነው መረጃ ለመረዳት ችለናል።

(በፎቶው ላይ የምትታየው ሳባ የአባይ ጸሐዬ የእንጀራ ልጅ ናት:: በቀደመው መረጃ ላይ የአባይ ጸሐዬ ልጅ ተብሎ ተዘግቦ ነበር:: :: ከአባይ ጸሐዬ ከሚወልዳት ቤቢ አባይ ጸሐዬ ጋር በ እናት ይገናኛሉ:: ስለ ሳባ ተጨማሪ መረጃዎችን ከመቀሌ እስከ ቻይና ያሉትን ከደቂቃዎች በኋላ ይዘን እንቀርባለን::)

ምንም እንኳ እንደ ሪፖርተር ያሉ የ ሥር ዓቱ ሚዲያዎች ሆን ብለው ባለቤታቸው አይደለችም እያሉ ለማስወራትና መረጃውን ለማደናገር ቢሞክሩም ሳሌም ከበደ ከወር በፊት በሙስና ተጠርጥራ መታሰርዋ የሚታወስ ሲሆን በእስር ላይ የሚገኙ ባለሀብቶችም ከአባይ ጸሃዬ ጋር ስላላችሁ የዝርፍያ ግንኙነት እየተናገሩ ይገኛሉ።

የኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሲዝቱ የነበሩት እኚህ ሰው ባለበታቸው በታሰሩ ግዜ የተለያዩ ጀኔራሎች ዘንድ በመደወል “አድኑኝ” እያሉ ሲማጸኑ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል።

በአሁን ሰዓት በህወሃት አመራር መካከል በተፈጠረው የከረረ ክፍፍል እና ያለመግባባት ሳብያ ስጋት ውስጥ የገቡት አቶ አባይ ጸሃዬ የተዘረፈውን የሃገርን ሃብት እና ልጆቻቸውን በሙሉ ከሃገር አሽሽተዋል።

ከአቶ አባይ ጸሃዬ ውጪ ጄነራል ሳሞራ የኑስ፣ ስብሃት ነጋ፣ አርከበ እቁባይ፣ ደብረጽዮን ገብረ ሚካአኤል፣ … በቢሊዮን የሚቆጠር የሕዝብ ገንዘብ እና ዘመድ አዝማዳቸውን በማሸሽ ላይ እንደሚገኙም የተጠቆመ ሲሆን አቶ ብርሃኔ ገብረ ክርስቶስ ወርደው የቻይና አምባሳደር እንዲሆኑ የተደረገው ለባለስልጣናቱ የመጨረሻ የማምለጫ አማራጭ ለማበጀት ነው ተብሏል።

በትግራይ ህዝብ ስም እየነገዱ ያሉት እነዚህ ጥቂት ሰዎች፣ ሃገሪቱን ለማስተዳደር ያልቻሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ አለም አቀፍ ሜዲያም እየተናገሩ ነው። የህወሃት ሰዎች በሁለት ጎራ ተከፍለው አሁን የማይወጡበት ችግር ውስጥ ስለገቡ ያላቸው አማራጭ ሃብት እና ዘመዶቻቸውን ማሸሽ በመሆኑ ይህንን ተያይዘውታል። በስሙ ሲነግዱበት የነበረውን የትግራይ ሕዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ እንዲጫረስ አድርገው እነሱ እግሬ አውጭኝ ማለታቸውን የትግራይ ሕዝብ ከወዲሁ ሊያወግዘው ይገባል።

****************************************************************************

ሳባ (የአባይ ጸሐዬ የእንጀራ ልጅ) ከ’ወዛመይ’ እስከ በቻይና የሚገኘው የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ባለቤትነት * ከሞላ አስገዶም ጋር ምን ታደርጋለች?

ሳባ በቻይና በተከፈተላት “ሳቢና የተሰኘው” ሬስቶራንቷ በር ላይ::

ከውስጥ አዋቂ ለዘ-ሐበሻ የተላከ መረጃ

በሕወሓት ውስጥ የተፈጠረው መፈረካከስ ያሰጋቸው ባለስልጣናት ልጆቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ወደ ውጭ ማሸሹን ተያይዘውታል:: በሙስና እስር ስጋት ውስጥ ያሉት አስራ ሁለቱ የአባይ ጸሐዬ ልጆች አሜሪካ ገብተዋል:: በሃገር ቤት የቀጠለው እርስ በ እርስ የሕወሓቶች መበላላት ጉዳዩ እስኪረጋጋ እዚህ ይቆያሉ:: ካልተረጋጉም እዚህ ያፈሩትን ንብረት ይዘው ይቀጥላሉ::

ከአባይ ጸሐዬ ልጆች መካከል አንዷ ቢቢ አንዷ ናት:: በአዲስ አበባ የ7 ህንጻዎች ባለቤት ናት:: በ እናት ከምትገናኛትና ለአባይ ጸሐዬ የ እንጀራ ልጅ ሳባ ወርቁ ጋር አብረው ዱባይ ቆይተው ሳባ ወደ ቻይና እንዲሁም ባቢ ከ12ቱ እህት ወንድሞቿ ጋር አሜሪካ ትገኛለች::(አቡዳቢ  ውስጥ ስለነበረውና ስላለው ጉዳይ ወደፊት ሰፋ ያለ መረጃ ይቀርባል)

ትናንት በዘገባዎች ላይ ሳባ የአባይ ጸሐዬ ልጅ ተብላ ከተለጠፈች በኋላ የሥርዓቱ ሰዎች “ሳባ የአባይ ልጅ አይደለችም” ለማለት ቃትቷቸው ነበር:: የእንጀራ አባት እንደ አባት ካልተቆጠረ አዎ አባቷ ላይሆን ይችላል:: ግን የአባይ ጸሐዬ ልጅ እህት ናት:: ለዚህም ነው ስለዚህች ወጣት ሚሊየነር ነገሮችን መረጃዎችን እንድንፈለፍል ያደረገን::

ሳራ ከሞላ አስገዶምና ከጓደኞቹ ጋር በመሸታ ቤት

ሳባ ወዛመይ የተሰኘው የዳዊት ነጋ የሙዚቃ ክሊፕ ትግራይ ውስጥ የሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ተቀርጿል:: በክሊፑ ላይም ተውናለች:: በጓደኞቿ ዘንድ “የወርቅ ዘር” በሚል የምትታማው ሳባ ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነትን ካሸነፈ በኋላ ሳቢና የተሰኘው ሬስቶራንት በቻይና የተሰኘ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ቻይና ውስጥ ተከፍቶላታል::

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃብትና ንብረት በየመሸታ ቤቱ አርቲስቶችን በመጋበዝ ይበተናል::

ቻይና በርካታ የሕወሃት ባለስልጣናት ልጆች እንደሚማሩ ይታወቃል:: በዚሁ ቻይና ውስጥ አምባሳደር ሲሾም እንኳ የሚሾመው ከሕወሓት ተመርጦ ነው:: በቻይና የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ይመላለሳሉ:: ይህ ሬስቶራንት ነጋዴዎች የሚሰለሉበት እንደሆነ የሚናገሩት የውስጥ ምንጮች ከኢምባሲው ጋር ብዙ የሚሰራቸው ምስጢራዊ ጉዳዮች እንዳሉ ምንጮቹ ይናገራሉ:: አብዛኞቹም የሚሰሩት ምስጢራዊ ነገሮች እናንተ አንባቢዎች የምትገምቱት ዓይነት ነው::

ሳባ ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ጋር ግንኙነት አላት:: በሃገር ቤት አርቲስቶችን ባገኘች ቁጥርም በየመሸታ ቤቱ ጋባዥ እርሷ ናት:: ዱባይ በነበረችበት ወቅትም ተዋቂ ሰዎች እዚያ ሲመጡ ተቀባይና ሃገር አሳይ በመሆን ጀርባቸው ምን እንዳለ የምታጠናው እርሷ ነበረች እየተባለ በሰፊው መረጃዎች ይነገሩባታል::

ሳባ መቀሌ በነበረችበት ወቅት

ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የገባው የትህዴን መሪ ሞላ አስገዶም ጋርም በተደጋጋሚ በየመሸታ ቤቱ መታየቷን የሚናገሩት ምንጮቹ ፎቶዎችን አስደግፈው ልከዋል:: ከሞላ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እስከምን ድረስ እንደሆነ የሚታወቅ ባይሆንም ሆኖም ግን አብረው በብዛት ታይተዋል::

ሳባ ዛሬ በስሟ ቻይና ውስጥ ሬስቶራንቱን ተከፍቶላት እየሰራች ነው:: የወደፊቱ የሕወሓት መሪዎች መኖሪያ በምትባለው ቻይና እንዲህ ያለው ሬስቶራንት መከፈቱ ጥቅሙ ለሕወሓት ሰዎች ሳይታለም የተፈታ ነው::

ቻይና ለንግድ የሚሄዱ ከሕወሓት ጋር ንክኪ የሌላቸው ነጋዴዎች ሊያስቡበት የሚገባውን ጉዳይ እዚህ ጋር ጠቆም አድርገናል::

__________________________
ተጨማሪ መረጃዎችን እያሰባሰብን ለሕዝብ እናቀርባለን::
በሌሎችም የውጭ ሃገራት የሚገኙ የህወሃት ባለስልጣናት ንብረቶችና መረጃዎች እየደረሱን ሲሆን እያጣራን ማቅረባችንን እንቀጥላለን::

 

 

 
 

 

 

Dm eri tv subscribe

Eritrean Memorial Day ምዓልቲ ስዉኣት ኤርትራ

Hdri Media Books on Amazon.com
visit hdrimedia.com