Dehai News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የቡሬ እና የድባይ ሲማ ድንበርን በይፋ ከፈቱ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Tuesday, 11 September 2018


ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የቡሬ እና የድባይ ሲማ ድንበርን በይፋ ከፈቱ




አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2018 (ኤፍ..) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የቡሬ – ድባይ ሲማ ድንበርን በይፋ ከፈቱ፡፡

ሁለቱ መሪዎች አዲስ ዓመትን ምክንት በማድረግ ነው ድንበሩን በይፋ የከፈቱት ተብሏል፡፡

የድንበሩ መከፈት በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የየብስ ትራንስፖርት ግንኙነት ዳግም እንዲጀምር ያስችለዋል፡፡

ከድንበሩ መከፈት በኋላም ሁለቱ መሪዎች ወደ አስመራ ማቅናታቸው ተገልጿል፡፡

የአስመራ ቆታቸውን እንዳጠናቀቁ ደግሞ ወደ ዛላምበሳ በማቅናት በተመሳሳይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዓመታት ተዘግቶ የቆየውን ድንበር በይፋ እንደሚከፍቱ ከኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአብርሃም ፈቀደ



EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events