Date: Thursday, 21 February 2019
የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ የማጠቃለያ ዝግጅት በሚሌኒየም አዳረሽ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ, የካቲት 21, 2019 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ የማጠቃለያ ዝግጅት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳረሽ እየተካሄደ ነው.
በአሁኑ ስዓትም የኤርትራ የባህል ቡድን አባላት በሚሊኒየም አዳራሽ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ስራዎቻቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ.
በዚሁ ስነ ስርዓት ላይም የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የኤርትራ አቻቸው ኡስማን ሳለህን ጨምሮ የተለያዩ የተለያዩ እንግዶች እንግዶች በመሳተፍ ይግኛሉ ይግኛሉ ይግኛሉ.
የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልዑካን በባህርዳር, በሀዋሳና አዳማ ከተሞች ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመወያየት የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎችን ማቅረባቸው ይታወቃል.
ልዑካኑ በእነዚህ ከተሞች በነበራቸው ቆይታም ከማህበረሰቡ የተለየ አቀባበልና ፍቅር የተቸራቸው መሆኑን ተናግረዋል.
የልኡካን ቡድኑ በዛሬው ዕለትም በኢትዮጵያ የሚኖረውን ቆይታ አጠናቆ ሽኝት የሚደረግለት ይሆናል.