Dehai

Goolgule.com: የትህነግ አዲሱ ሤራ – አማራን በውክልና እልህ ውስጥ መክተት

Posted by: Berhane.Habtemariam59@web.de

Date: Monday, 19 October 2020

* የአማራ ክልል ሰላም መሆን ለትህነግ ሤራ ስኬት ዕንቅፋት መሆኑ ተገመገመ  

By

ስብሃት ነጋ የሚባለው የትህነግ (ህወሃት) ማፊያ ቡድን አውራ ገና ወደ በረሃ ከመግባቱ በፊት አዲስ አበባ ፒያሳ ከገብረ ትንሳኤ ኬክ ቤት ዝቅ ብሎ ፍሎሪዳ ቡና ቤት መጠጥ ጠግቦ ሲወጣ ሽንት ያዘው። ከዚያም ከፍሎሪዳ እንደወጣ ያለው አደባባይ ላይ ለመሽናት አብሮት ከነበረው ባልደረባው ጋር በመሆን በሞቅታ እያወጋ ተጠጋ። አደባባዩ ላይ ሲሸና እየገለፈጠ “አማራ ላይ እንሽና” ማለቱን በወቅቱ አብሮት ከነበረው ሰው በጀብድ ሲወራ መስማቱን የመረጃ ምንጫችን ይናገራል።  

ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ብሎ በመሰየም አገር ሲያተራምስና ሲዘርፍ ኖሮ መንግሥት እንዲሆን ባዕዳን ኢትዮጵያ አናት ላይ አስቀምጠውት የነበረው የጥቂት ወንበዴዎች ጥርቅም ከጅምሩ የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት የተነሳ በመሆኑ ከላይ የተገለጸውን ሃሳብ መጠራጠር አይቻልም።  

የሕዝብ ቁጣና መንገፍገፍ፣ አጋር ሆነው አብረውት ይሠሩ በነበሩ ለኅሊናቸው የቀረቡ ታጋዮች ኃይል የተሽቀነጠረው ትህነግ፤ “ዲጂታል ወያኔ” በሚል አንድ በገሃድ የተደራጀ ኃይል ይዞ ብቅ አለ። ይህ በበጀት፣ በሰው ኃይልና አጀንዳ በሚያዘጋጁ የትህነግ ቧለሟሎች የሚመራና በበላይ ጠባቂነት ደብረጽዮን የሚቆጣጠረው የሳይበር ጦር፤ ትህነግ ተመልሶ ኢትዮጵያን እንዳሻው እንዲጋልብ አልሞ ዘመቻውን ጀመረ። በሺህዎች በሚቆጠሩ የዲጂታል ወያኔ አባላት አማካኝነት የፈጠራ መረጃውን በማሰራጨት አገር ማተራመሱን ተያያዘ። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በየዕለቱ አገራዊ መረጃ የሚሰበስበው ሕዝብ የዚህ የሐሰትና የተዛባ መረጃ ሰለባ ሆነ።  

ቀደም ብለን ለዚሁ የሳይበር ወንበዴዎች ቡድን ቅርብ የሆነ ወጣት ጠቅሰን እንደዘገብነው ዋናው የዘመቻው ማጠንጠኛ የአማራ ህዝብና ዶ/ር ዐቢይ ናቸው። በተመሳሳይ አጀንዳ ቀደም ሲል ይህንኑ የመረጃ ምንጫችንን ጠቅሰን እንደዘገብነው “እረኛውን ግደል መንጋው ይበተናል” በሚለው የወንበዴው የሳይበር ዘመቻ ዶ/ር ዐቢይን ከሕዝብ ለመነጠል የተረጨው የማጠልሸት ዘመቻ በውጤት ደረጃ እጅግ ስኬት ማስመዝገቡን በግምገማ አረጋገጡ።  

ከግምገማው በኋላ እንደ አቅጣጫ የተቀመጠው “ሕዝብ ወያኔ ይሻላል እያለ ነው። ዳግም ወደ አመራር ተመልሰን አገሪቱን እንድናረጋጋ ጥያቄ ቀርቦልናል” የሚሉና ሌሎች ተመሳሳይ ቅስቀሳዎችን በማሰራጨት ወደ ቀጣዩ የትግል ምዕራፍ ለመሸጋገር ተወሰነ።  

ትህነግ ለይቶ ዶ/ር ዐቢይ ላይ ዘመቻ መክፈቱ፣ ዘመቻውም በስኬት መገምገሙ የራሱ እንደምታ ያለው ጉዳይ ቢሆንም፣ ትህነግ ከዚሁ ጎን ለጎን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የውክልና አተራማሾችን በዘረፋ ያከማቸውን ከፍተኛ ሃብት በማሰራጨት አሰማርቶ ህዝብ ሰላም እንዳይሰማው ማድረጉንም በተመሳሳይ በስኬት እንደገመገመ ይኸው የጎልጉል መረጃ አቀባይ አስታውቋል።  

በአማራ፣ በኦሮሞና በታቦትና ቅዱሳን መገለጫዎች በማኅበራዊ ሚዲያ የተበተኑት የሳይበር ጭፍሮች፣ ታልሞና ታስቦበት ከበላዮቻቸው የሚሰጣቸውን የዓላማ ማስፈጸሚያ አጀንዳ “ሳያኝኩ የሚውጡ” ሼር ማድረጋቸው ትልቁ ችግር መሆኑ ቢገለጽም ዜጎች ሊማሩ አለመቻላቸው አሳዛኝ እንደሆነ ጉሊና ይሄይስ የተባሉ ተከታታያችን በወቅቱ በአጭር መልዕት ሳጥን ልከውልን እንደነበር መግለጹ ለአሁን አስፈላጊ በመሆኑ ጠቅሰነዋል።  

ጉሊና አንድ ገጠመኛቸውን አክለዋል “አንድ የማውቃት የትህነግ ደጋፊና ጽንፈኛ አቀንቃኝ ጓደኛ ነበረችኝ። ከትህነግ ታዋቂ ሰዎች የአንዱ ሚስት ነበረች። እንዴት እንደተመቻቸላት ሙሉ መረጃ ባይኖረኝም ዛሬ አሜሪካ ንብረት ገዝታ ትኖራለሽ። አመጹ በተቀጣጠለበት ወቅት ‘ኦሮሞ በትግሬዎች ዘንድ እንደ ሰው አይቆጠርም። አንድ ትግሬ ኦሮሞ ካገባ ይናቃል’ ትለኝ ነበር። አንድ ቀን በድንገት የኦሮሞ ተቆርቋሪ ሆና አገኘኋት። ምን ተገኘ በሚል ስጠይቃት ‘ፖለቲካ ነው። እኛ በስሜት አንነዳም። የትግልና የግንኙነት መስመር አለን’ አለችኝ። ግንኙነታቸን ብዙ ስለሚያጫውተን በርካታ ነገር ብላኛለች። ይህንን ቀንጥቤ የላኩት የሚሰማ ካለ ከስሜት እንዲላቀቅ ብታደርሱ ብዬ ነው” ሲሉ በመልዕክት ሳጥናችን አስፍረዋል።  

የጎልጉል መረጃ አቀባይ ሰሞኑንን በነገሩን መሠረት የህወሃት ደጋፊዋ ሴት “እኛ በስሜት አንነዳም” ከማለቷ ጋር ዝምድና ያለው ነው። እንደ መረጃው ሰው ዲጂታል ወያኔ የሚባለው የሳይበር ወንበዴዎች ጭፍራ አማራን አልሞ አዲስ ሤራ ተግባራዊ እያደረገ ነው።  

ይህ የሆነው አንዱ የዲጂታል ወያኔ ጭፍራ የመስመር መኮንን ዳንኤል ብርሃኔ “ከመስከረም በኋላ የሚሆነውን ጠብቁ፤ ዐቢይ በዘር ማጥፋት በቅርቡ ለፍርድ ይቀርባል…” እያለ ሲያሰራጭ እንደነበረው፣ ልደቱና እነ ጃዋር በተደጋጋሚ እንዳስረዱት ከመስከረም በፊት መንግሥትን ለማሽቀንጠር በትሥሥር ከፍተኛ ሃብት ፈስሶ የተነደፈው ዕቅድ እንዴት ከሸፈ በሚል ግምገማ ከተደረገ በኋላ ነው።  

በዚሁ ግምገማ መሠረት የትህነግ ኃላፊዎች በስብሃት ነጋ መሪነት ባደረጉት ግምገማ “አማራው ክልል ሰላም መሆኑ ዕቅዳችን እንዳይሳካ አድርጓል” የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። እንደ መፍትሄ ያቀረቡት ይህን ከጅምሩ ሊያጠፉት በመታገያ ደብተራቸው ላይ በጠላትነት የፈረጁትን ሕዝብ በግድያ፣ በጥቃት፣ በትንኮሳ፣ ወዘተ ትዕግስቱ እንዲያልቅ ማድረግ ነው። ትዕግስቱ ሲያልቅና በተለይ በማንነቴ ላይ የተቃጣውን እመክታለሁ በማለት ወደ ኃይል ርምጃ ሲገባ አገሪቱ ትተራመሳለች። ስለዚህም ይህ ይሆን ዘንድ ምን መደረግ አለበት ተብሎ አዲስ ዕቅድ በማፊያው ቡድን ህወሃት ተነድፏል።  

እነ ጃዋርን አቅፎ የተነደፈውና እነ በቀለ ገርባ ትግራይ የተመላለሱበት፣ ዳውድ ኢብሳ አመራራቸውን ትግራይ ድረስ ሲያመላልሱ የነበረበት፣ አንዳንዶቹ የወጣት ሊግ አመራሮቻቸውን ወደ መቀሌ የላኩበት፣ በወላይታ፣ በቅማንትና በአገው ሕዝብ ውስጥ ሲሠራ የነበረው የተቀነባበረ ሤራ ህወሃት የበጀተውን ሃብት ቀርጥፎ ህልም በመሆኑ አማራ ክልልን ካልተተራመሰ ትህነግ ያሻውን እንደማያሳካ ታምኗል።  

ለዚህ ነው በቤኒሻንጉል ንጹሃን የአማራና የአገው ተወላጆች የሚገደሉት። በተደጋጋሚ ንጹሃን ላይ ዕልቂት እንዲፈጸም የሚያቀናብሩት ቤኒሻንጉል የተቀመጡ የትግራይ ኢንቨስት አድራጊ ተብዬዎች እንደሆኑም የሁለቱም ክልል መሪዎች በይፋ መናገራቸው የመረጃውን ሰው ትክክለኛነት ያሳያል። ሌላው ማሳያ በቤኒሻንጉል የሚፈጸመውን ግድያ በምስል በማስደገፍ የትህነግ ሚዲያዎችና የዲጂታል ወያኔ ጭፍራዎች መበተናቸው ነው። ጉሊና እንዳሉት መረጃ ሳያኝኩ የሚወጡ ግማሹ ለከንቱ ክሊክና ሳንቲም ለቀማ፣ ሌሎች ደግሞ በቁጭትና ሀዘን ሼር እያደረጉ ያሰራጩታል። በውጤቱም የአማራ ህዝብና አመራሮች አሁን እየታየ እንዳለው ወደ ንዴትና እልህ እያመሩ እርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ላይ መድረሳቸውን በማወጅ ላይ እንዲደርሱ እያደረጋቸው ሆኖ ታይቷል።  

ይህ ብቻ አይደለም አማራውን ወደ እልህ የሚከቱ በርካታ ዕቅዶች አሉ። አንዱን ዕቅድ በሌላኛው በማጀብ የሚተገበረው ይህ አማራውን አበሳጭቶ ወደ ግጭት የመንዳት አካሄድ ከፍቼ እስከ ሱሉልታ ባለው መንግድ በቅርቡ የታጠቁ የኦሮሚያ ኃይሎች ፈጸሙት የሚባለው ህገወጥ ድርጊትና ግድያ ሌላው ዕቅድ ነው።  

ከቅርብ ወራት ወዲህ ከአማራ ክልል በደጀን መስመር ወደ አዲስ አባባ የሚሄዱና የሚመለሱ ከባድ የደረቅ የጭነት ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከጎሐጽዮን ደብረጉራቻ ባለው መስመር ማለፍ ፈተና ሆኖባቸዋል።

አስተያየታቸውን ከሰጡት አሽከርካሪዎች መካከል አንዱ “ከፍቼ ከተማ የቅርብ ርቀት ከምትገኝ ‘አሊ ዶሮ’ ከተባለች ቦታ ላይ መስከረም 30/2013 ዓም የክልሉን የፀጥታ ኃይሎች የደንብ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው የቆሰሉና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አሽከርካሪዎችና ከ10 በላይ የተሰባበሩና የተቃጠሉ መኪናዎች አሉ” ብሏል። የሞቱም እንዳሉ ተዘግቧል

“ጠላትም ወዳጅም ይስማ” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን በፌስቡክ ገጻቸው ከትናንት በስቲያ እንዳሉት ካሁን በኋላ ማንም ይሁን ማን አጸፋ እንደሚመለስ መናገራቸው፤ የጸጥታው ዘርፍ ላይ የሚሰሩ በተደጋጋሚ ስሜታቸው መጎዳቱንና እርምጃ እንዲወሰድ የሚገፋፉ ሃሳቦችን በአማራ ሚዲያ ማሰራጨታቸው ምናልባትም ሳያስቡት ትህነግ ባስቀመጠው የመጨረሻው ባቡር መሳፈር እንዳይሆን የመረጃው ምንጫችን ስጋቱን ይገልጻል።

ከሃጫሉ ሁንዴሣ ግድያ በኋላ በሻሸመኔና ሌሎች አካባቢዎች ሰዎች በማንነታቸው በግፍ መጨፍጨፋቸው “አማራው ራሱን ይከላከል” የሚለውን ሃሳብ እያጎላው ከመጣ ሰነባብቷል። ይህንንም ተከትሎ ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ቤተክርስቲያን ራሷ መከላከል አለባት በማለት ሲናገሩ በአዳራሹ የነበረው ተሰብሳቢ ሞቅ ባለ ጭብጨባ ማገዙ ፓትርያርኩ በጉዳይ ፈጻሚነት ይሁን ከቁጭት በመነሳት መናገራቸው ባይታወቅም ትኩረት የሳበ ሆኗል።

የመተከሉን በህወሃት የተቀነባበረና በሎጂስቲክስ የታገዘ የግፍ ግድያ ተከትሎ ምክትል ጠ/ሚ/ር ደመቀ መኮንን “ልብ ሰባሪ” ነው ያሉትን ጥቃት ለመከላከል የአካባቢው ሕዝብ ተደራጅቶና ታጥቆ ራሱን መከላከል አለበት ማለታቸው “አማራን እልህ በማስጨረስ የአጸፋ ጥቃት ውስጥ ማስገባት” ወደሚለው የህወሃት የሤራ ቀለበት በቁጭት ሰበብ አስገብቷቸው ይሆን የሚያስብል ሆኗል።    

የገንዘብ ለውጡን ተከትሎ ትህነግ ጉሮሮው እየታነቀና እንደ ቁስል እየነቃ ስለሆነ ይህ የመጨረሻው ዕቅድ ሊሆን እንደሚችል በርካቶች ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። በዚህም ሳቢያ የአማራ ክልል የሚያደርገውን ሁሉ ከስሜት በጸዳ አግባብ እንዲያከናውን ምክር የሚሰጡም ጥቂት አይደሉም።  

ትህነግ ይህንን ዓላማ ለማሳካት በርካታ ርቀት ልትሄድ እንደምትችል የሚጠቁመው የጎልጉል የመረጃ አቀባይ በቅርቡ በሃይማኖት ተቋማት የቀረበው ተነስ ታጠቅ ምን አልባትም የዚሁ አማራውን ጎትጉቶ ቃታ እንዲስብና አገሪቱ እንድትወላልቅ ማድረግ፣ ከዚያም በሰላም ማስከበር ስም ትህነግ ዳግም ህልሙን ዕውን ሊያደርግ ያሰበበት ረቂቅ ሤራ ሊሆን የመቻሉ ጉዳይ በጥንቃቄ መታየት የሚገባው ነው።

የኅልውና ጉዳይ፤ የመኖርና ያለመኖር አጣብቂኝ ውስጥ ያለው የአማራ ሕዝብ ከእንግዲህ ወዲህ ተደራጅቶና ታጥቆ ራሱን መከላከል እንዳለበት በመርህ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ጉዳይ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ርምጃ ሲወስድ ግን ለዚህ ሁሉ ግፍ ያበቃውንና “ጠላቴ ነህ” ብሎ የሰየመውን ህወሃትን፤ “አማራ ላይ እንሽና” በማለት ከተናገረው የበረኻ ወንበዴዎቹ ዋና አምበል ስብሃት ነጋን ታሳቢ በማድረግ፣ በሰከነ እና ጥቅምና ጉዳቱን፤ ግራና ቀኙን በጥሞና ባገናዘበ መልኩ ሊሆን እንደሚገባው የሚስማሙ ጥቂቶች አይደሉም።   


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events