Dehai News

(አሚኮ)"በትግራይ ክልል በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል" የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን

Posted by: Semere Asmelash

Date: Tuesday, 13 July 2021

"በትግራይ ክልል በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል" የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በትግራይ ክልል በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት በእጅጉ እንዳሳሰባቸው በመግለጽ በአስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባ አሳሰቡ።

ኮሚሽነሩ በትግራይ ክልል የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ደህንነትን በተመለከተ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም በትግራይ ክልል የተካሄደው የሰላም ማስከበር ዘመቻ ከተጀመረ አንስቶ ስደተኞቹ በሁለት ተዋጊ አካላት መሃል ለመውደቅ መገደዳቸውን፣ ሁለት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች መውደማቸውን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሕይወታቸውን ለማትረፍ ዳግም ለመሰደድ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ኤርትራውያን ስደተኞች በአንድ ወይም ሌላ ወገን ደጋፊነት ተፈርጀው የበቀል ጥቃት እየደረሰባቸው እንዲሁም ተጠልፈው እየተወሰዱ እና እየተያዙ ስለመሆኑ የተጣሩ እና በማስረጃ የተደገፉ ሪፖርቶች ለኮሚሽኑ መድረሳቸውንም ተናግረዋል።

በማይ አይኒ እና በአዲ ሃሩሽ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በሚገኙ ስደተኞች ላይ በተለያዩ ታጣቂዎች በተለይ ማታ ማታ የሚፈፀሙ አጠቃላይ የወንጀል ድርጊቶች በእጅጉ ረብሸውኛል ብለዋል ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ።

ባለፉት ሳምንታት ሽሬ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ለእስር ተዳርገዋል ያሉት ኮሚሽነሩ፣ በመቐለ የሚገኙ አካላት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ እንዲሁም በሕገ-ወጥ መንገድ የታሰሩ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ መጠየቃቸውን ጠቁመዋል።

ከዚህም ባሻገር በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ በጣም ከባድ የሆኑ የኃይል ጥቃቶች እየደረሱ ስለመሆኑ የሚጠቁሙ ሪፖርቶች እየወጡ በመሆኑ፣ የፌደራል መንግሥትም ሆነ በትግራይ ክልል ያሉ አካላት በእነዚህ ተዓማኒ ክሶች ላይ መደበኛ ምርመራ እንዲጀምሩ ጥሪ ማቅረባቸውንም ገልጸዋል።

ስደተኞች ድጋፍ የሚሹ እና ዓለም አቀፍ ከለላ የማግኘት መብት ያላቸው ሲቪል በመሆናቸው በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የሚደርስው ጥቃት እና ማስፈራራት በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Bir bir veya daha fazla kişi, ayakta duran insanlar, açık hava ve şunu diyen bir yazı 'UNHCR The UN Refugee Agency ABOUT US Media centre EMERGENCIES Refworld Data DONATE DO YOU NEED HELP? Supply Chain WHAT WE DO Home NEWS AND STORIES News and Stories Careers Search OUR PARTNERS Press Releases Glo GET INVOLVED Statement by UN High Commissioner for Refugees Filippo Grandi on the situation of Eritrean refugees in Ethiopia's Tigray Region 13 July 2021 Français' görseli olabilir


EmbassyMedia - ራብዓይ ግንባር!

Dehai Events