ሰበር ዜና-አምቦ እስካሁን 10 ሰዎች በአጋዚ መገደላቸው ታወቀ – ቁጥሩ ከፍ ሊል ይችላል – ፖሊሶች የዳንጎቴ ትራክ ሲያቃጥሉ ታይተዋል
October 26, 2017 |
ዜናው ተመልከተው፡
ESAT Special News Ambo Protest 26 October 2017
(ዘ-ሐበሻ) አምቦ ከተማ ዛሬ ጠዋት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ መንግስት በከፈተው ተኩስ እስካሁን የአስር ሰዎች ሕይወት ማለፉን የከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጋዲሳ ደሳለኝ ተናገሩ:: እንደ አቶ ጋዲሳ ገለጻ ተኩሱን የከፈተው የአጋዚ ኃይል ነው::

በአቶ ጋዲሳ መረጃ መሰረት በተኩሱ 20 ሰዎች እንደቆሰሉ ተናግረዋል::
በአምቦ ከተማ በተደረገው ተቃውሞ ትንሽ የማይባሉ መኪኖች መቃጠላቸው ሲዘገብ በተለይም የናይጄሪያዊው ባለሃብት ንብረት የሆነው ዳንጎቴ ሲሚንቶ ንብረት የሆነ ትራክ በፌደራል ፖሊሶች ሲቃጠሉ ማየታቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል:: የፌደራል ፖሊስ ካቃጠላቸው በኋላም እዚያው ቦታ ላይ 3 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እነዚሁ እማኞች ይናገራሉ::
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነው ስዩም ተሾመ በበኩሉ “የመከላከያ ሰራዊት ወደ አምቦ ከተማ እየገባ ነው፡፡ አሁን ላይ በደረሰኝ መረጃ መሠረት መከላከያ ሰራዊቱ Goal project በሚባለው የከተማው መግቢያ የደረሰ ሲሆን፣ ከአቅራቢያው ተደጋጋሚ የጥይት ተኩስ ይሰማል” ሲል ጽፏል::
ስዩም አክሉም “አምቦ ወደሚገኙ አምስት ሰዎች ጋር ደወልኩ፡፡ የሁሉም ሰዎች ስልክ ይጠራል ግን አያነሱም!! በInbox እንደነገሩኝ ከሆነ “በአሁን ሰዓት በከተማው ውስጥ #ስልክ ማናገር ለአደጋ ያጋልጣል” ብለውኛል፡፡ አሁን አምቦ ያለችበትን ሁኔታ የሚያሳዩ የሚከተሉትን ፎቶዎች ልከውልኛል፡፡ በእርግጥ አምቦ የጦር አውድማ ሆናለች!!” ሲል ከስፍራው ዘግቧል::
የአምቦውን ሁኔታ እየተከታተልን እንዘግባለን::
*****************************************************************************
የሰው ሕይወት የተቀጠፈበት የአምቦ የተቃውሞ ውሎ በቢቢሲ ዘገባ
October 26, 2017 |
በግጭቱ ቢያንስ 10 ሰዎች እንደተገደሉ የአይን እማኞች ይናገራሉ
(Photo credit – BBC)
ስለአምቦው ውሎ የቢቢሲ ዘገባ እንደወረደ:-
በስልክ ያነጋገርናቸው የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች እንደነገሩን ስኳር ጭነው በከተማው የሚያልፉ መኪኖች እንዳሉ መረጃ ለአካባቢው በመድረሱ ፤ መኪኖቹን ለማስቆም በመጠባበቅ ከትናንት ጀምሮ መንገድ መዝጋት ጀምረው ነበር።
ምክንያታቸው ደግሞ በሀገሪቱ የሚታየው የስኳር እጥረት በአምቦም የሚስተዋል መሆኑ ነው።
በከተማዋ አንድ ኪሎ እሰከ 70 ብር ድረስ ይሸጣል ይላሉ።
እናም በዚህ ሁኔታ ስኳር ተጭኖ ወደሌላ ቦታ መሄዱን በመቃወም ነው መንገድ መዝጋት የጀመሩት።
” ከተማዋን አቆርጠው የሚሄዱ ዋናና መጋቢ መንገዶች በመዘጋታቸው የክልሉ ፖሊስና እኛ ሆነን በህገወጥ መንገድ ሊያልፍ የነበረውን ስኳር ስንጠብቅ አድረናል”ይላሉ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለገ አንድ የአካባቢው ነዋሪ።
ዛሬ ግን ከማለዳው አንድ ሰዓት አካባቢ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት መለያ የለበሱ በተቃዋሚዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን ተናግሯል።
“እኔ በአይኔ ያየሁት አምስት ሰዎች ሲገደሉ ነው።ግን የሞቱት በጣም በርካታ ሰዎች ናቸው” ያለን ደግሞ ሌላው የከተማዋ ነዋሪ ነው።
” ሁለት የፌደራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ በድንጋይ ተደብድበው እንደሞቱ አይቻለሁ” ብሎናል።
ቢቢሲ ግን የሟቾቹን ትክክለኛ ቁጥር ለማረጋገጥ አልቻለም። ከግጭቱ ጋር ተያይዞ በንብረት ላይም ጉዳት የደረሰ ሲሆን የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ንብረት የሆኑ ሁለት የጭነት መኪናዎች ተቃጥለዋል።
በከተማዋ ስኳር እንዳይዘዋወር መንገዶች እንዲህ ተዘግተዋል
የአሮሚያ ክልል የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ አዲሱ አረጋ በፌስ ቡክ ገጻቸው የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በሌሎች ሰዎች ላይም የአካል ጉዳት መደረሱን የሚገልጽ መረጃ አስፍረዋል።
” ከሰላማዊ ሰልፍና ከስኳር ፍተሻ ጋር በተያያዘ ወጣቶችን በማነሳሳትና ስርዓት አልበኝነት እንዲስፋፋ በማድረግ ለግጭቱ መንስዔ የሆኑትን አካላት እናወግዛለን” ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት ከተማዋ በአንጻራዊነት የተረጋጋች ትመስላለች፤ ነገር ግን መንገዶች እንደተዘጉ ሲሆን ሰልፈኞቹም ወደየቤታቸው አልተመለሱም።
ከዚህም የተነሳ ብዙዎች አሁንም ተጨማሪ ጉዳት ሊደርስ የሚችል ስጋት እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
*****************************************************************************
Anti-government protest in central Ethiopia, Ambo town
Posted by: ecadforum
October 26, 2017
Anti-government protest continue for 2nd day in central Ethiopia, Oromia region Ambo town. About ten people have been killed after the notorious Ethiopian regime forces (Agazi) arrived in the city.
Watch: Anti-government protest in central Ethiopia, Ambo town
https://www.youtube.com/embed/z3liVqQXo7I
******************************************************************************
የሀገሪቱ ጦር እና ደህንነት የህወሓትን ስልጣን በማዳን ስራ ላይ አተኩሯል
October 26, 2017 |
(ቢቢኤን) በኢትዮጵያ የሚገኙው ማንኛውም ዓይነት ጦር እና የደህንነት አካል የህወሓትን ስልጣን ለመታደግ አተኩሮ እየሰረ እንደሚገኝ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የሀገሪቱ የደህንነት እና የመከላከያ ሰራዊት ቁልፍ ቦታዎች በህወሓት እጅ ውስጥ እንደመገኘቱ፣ የፓርቲውን ዕድሜ ለማራዘም ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተሰራ እንደሚገኝ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ለዚህም ሲባል መደበኛ ስራቸው ሀገር መጠበቅ የሆነ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህዝባዊ ተቃውሞ በተነሳባቸው ቦታዎች ጭምር እየሔዱ በህዝብ ላይ ጥቃት እየፈጸሙ እንደሚገኙ መረጃዎች በመጠቆም ላይ ናቸው፡፡

ከሁለቱ አካላት በተጨማሪ ደግሞ በህወሓት ርዕዮተ-ዓለም ቅርጽ የተመሰረተው የአጋዚ ጦርም እንደተለመደው፣ የስርዓቱን ዕድሜ ለማስቀጠል ግድያን ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት አረመኔያዊ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ከዚህ ቀደም ከነበረው አኳኃኑ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ እና ለተቃውሞ አደባባይ ከሚወጡ ሰዎች ጋር መግባባት መፍጠሩ ህወሓትን አላስደሰተውም ይላሉ- ታዛቢዎች፡፡ ለዚህም ሲባል የአጋዚ ጦር ተቃውሞ በሚነሳባቸው የኦሮሚያ ከተሞች እየገባ ግድያ እንዲፈጽም እየተደረገ ይገኛል ብለዋል-ታዛቢዎቹ፡፡
የህወሓት መንግስት ጀምበር እየጠለቀችበት እንደሚገኝ የሚናገሩ አስተያየት ሰጪዎች፣ ስርዓቱ የባከነ ሰዓት ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ ማንኛውንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ እንደማይመለስ ያክላሉ፡፡ ቀስ በቀስም ሀገሪቱን ወደ ወታደራዊ ስርዓት ሊወስዳት እንደሚችልም አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡ በተለይ በህወሓት እጅ የሚገኙት ዋና ዋና የደህንነት እና የመከላከያ ቦታዎች፣ አሁን ላይ ስርዓቱ እንዴት ብሎ ከመጣበት ህዝባዊ መዓት ማምለጥ እንዳለበት በሰፊው እየመከሩ እንደሆነ ከምንጮች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በየቀኑ እየተካሔዱ ባሉ ተቃውሞዎች የተነሳ ፋታ ያጣው የህወሓት መንግስት፣ አሁን ላይ ሌሎችን ገድሎ ራሱን ለማዳን እየተፍጨረጨረ ይገኛል፡፡