Dehai News

Zehabesha.com: ‘ወያኔ ሌባ ነው…’ – የእሬቻ በዓል ላይ የተሰማውን ተቃውሞ የሚያሳይ የ15 ደቂቃ ቪዲዮ ይዘናል

Posted by: Berhane Habtemariam

Date: Sunday, 01 October 2017

‘ወያኔ ሌባ ነው…’ – የእሬቻ በዓል ላይ የተሰማውን ተቃውሞ የሚያሳይ የ15 ደቂቃ ቪዲዮ ይዘናል

Watch:

https://www.youtube.com/embed/S6kL1NA9LWQ
‘ወያኔ ሌባ ነው…’ – የ እሬቻ በዓል ላይ የተሰማውን ተቃውሞ የሚያሳይ የ15 ደቂቃ ቪዲዮ ይዘናል

************************************************************

በዛሬው የኢሬቻ በዓል የተሳተፉ ወጣቶች በከፍተኛ ድምጽ የተቃውሞ መፈክሮች ሲያሰሙ ነበር::

ተስፋለም ወልደየስ

Watch:

ከመፈክሮቻቸው ውስጥ “ዶ/ር መረራ፣ በቀለ ገርባ ይፈቱ” ፣ “ኦሮሞዎችን መግደል ይቁም” የሚሉ ይገኙበታል። በበዓሉ ከተደመጡ መፈክሮች መካከል “ጭቆና በቃን፣ ለኦሮሞዎች ከሶማሌ ክልል መፈናቀል ምክንያት የሆኑ ለፍርድ ይቅረቡ፣ ነፃነት ለኦሮሚያ” የሚሉ ነበሩበት። የበዓሉ ታዳሚ ወጣቶች ተቃውሟቸውን በመፈክር እና በዘፈን ከማሰማታቸው ባሻገር ባለፈው ዓመት ህይወታቸውን ያጡ ዜጎችን ለማስታወስ ተንበርክከው፣ እጃቸውን በ”X” ምልክት በማጣመር ሀዘናቸውን ገልጸዋል። በስፍራው የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ፖሊሶች ተቃውሞውን በዝምታ አልፈውታል። ጸጥታ ለማስጠበቅ ከተሰማሩ ወጣቶች ጋር በመሆንም ሁኔታውን ለማረጋጋት እና በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በድምጽ ማጉያ መልዕክት ሲያስተላልፉ ታይተዋል።

(ፎቶ- ከተስፋለም ወልደየስ ማኅደር)

 
 
 

 

 
 

 

Leave a Reply


ፈንቅል - 1ይ ክፋል | Fenkil (Part 1) - ERi-TV Documentary

Dehai Events



Latest Posts