Dehai News

(ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ሰመረ ርእሶም በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

Posted by: Semere Asmelash

Date: Monday, 23 July 2018

አቶ ሰመረ ርእሶም በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

አቶ ሰመረ ርእሶም በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2018 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ሰመረ ርእሶም በኤርትራው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ።

አቶ ሰመረ ርእሶም በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሆነው እስከ ተሾሙበት ጊዜ ድረስ የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስትር ሆነው እያገለገሉ መቆየተቻውን የሀገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገ/መስቀል አስታውቀዋል።

አቶ ሰመረ ርእሶም  ከዚህ በፊት  በአሜሪካ የኤርትራ አምባሳደር ሆነው ማገልገላቸው  ተገልጿል።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ያደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ተከትሎ ባለፈው ሰኞ ኤርትራ ከ20 በኋላ በኢትዮጵያ ኢምባሲዋን መክፈቷ የሚታወስ ነው።

ይህንም ተከትሎ ባለፈው ዕሮብ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከ20 ዓመታት በኋላ በኤርትራ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወቅቱ አስታውቋል።

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከ20 ዓመት በኋላ   መጀመሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በረራ የጀመረ ሲሆን፥ በቅርቡም ወደ ምፅዋና አሰብ አየር መንገዱ በረራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።



አቶ ሰመረ ርእሶም በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

ፈንቅል - 1ይ ክፋል | Fenkil (Part 1) - ERi-TV Documentary

Dehai Events