አዲስ አበባ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የኤርትራ የነፃነት ቀንን አስመልክተው ለሀገሪቱ መንግስት እና ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ መንግስት ያለውን ቁርጠኝት አረጋግጠዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ በኢትዮጵያ ለኤርትራ ኤምባሲ በላኩት ደብዳቤ፥ ለኤርትራ መንግሥት እና ሕዝብ ሰላም እና ብልፅግና እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን፥ የኤርትራን የነፃነት ቀን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም፥ ወንድማማች የሆኑት ሁለቱ ሀገራት ያላቸው ትብብር የሀገራቱን እድገት እንደሚያፋጥን እና ሕዝቦቹንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
ለኤርትራ መንግሥት እና ሕዝብ ሰላም፣ ፍቅር እና ስኬትን መመኘታቸውንም የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡